loading
ኢትዮጵያ አየር ላይ ያለ እርጥበትን ወደ ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚቀይረውን ቴክኖሎጂ ከህንድ ለመዉሰድ ዝግጅት እያደረኩ ነዉ አለች

አርትስ 20/03/2011

ቴክኖሎጂዉን ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ  ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ  እና በኢትዮጵያ የህንድአምባሳደር አኑራግ ስሪቫስታቫ ተወያይተዋል፡፡

በዉይታቸዉ ወቅትም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ  የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ወደፊት በሚያራምዱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ በትኩረትእየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ህንድ በተለይ አየር ላይ ያለ እርጥበትን ወደ ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚቀይር ቴክኖሎጂን በመጠቀም ውሃ ታገኛለች፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  በድረገጹ እንዳስታወቀዉ ፤ከህንድ የቴክኖሎጂ ዉጤት ኢትዮጵያ ልምድ እንድትቀስምም በ2011 ዓ.ም ሚያዝያ ወርላይ የህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኢግዚቢሽን በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከህንድ ኢንባሲ ጋር በመተባበር በህንድ የጎላ ጠቀሜታ ያላቸውን የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ  ዉጤቶች  ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ የሚያካሄዱት ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *