አልበሽር የሱዳንና የቱርክ ትስስራቸው ታሪካዊም ሀይማኖታዊም ነው አሉ
አልበሽር የሱዳንና የቱርክ ትስስራቸው ታሪካዊም ሀይማኖታዊም ነው አሉ
አርትስ 13/03/2011
ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ይህን ያሉት የቱርኩን ምክትል ፕሬዝዳንት ፋውድ ኦክታይን ካርቱም ውስጥ ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው፡፡
አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበው ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ ጊዜያት የገቧቸውን ስምምነቶች ተግባራዊ ለማድረግ ያላቸው ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡
በአሁኑ ቱርክ ሱዳን ውስጥ በግብርና፣ በማእድን ፍለጋና በተለይ በወርቅና በነዳጅ ዘርፍ ኢንቨስት ለማድረግ መዘጋጀቷን የሱዳን የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ካርቱም እና አንካራ በዲፕሎማሲውም ሆነ በኢኮኖሚው መስክ ግንኙነታቸው ከፍ ወዳለ ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡
ይህ የሆነው ደግሞ ፕሬዝዳንት ኤርዶሀን 200 የንግድ ልኡካንን አስከትለው ሱዳንን ከጎበኙና ከ20 በላይ ስምምነቶችን ከፈረሙ በኋላ ነው ተብሏል፡፡