በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የራድዮሎጂ ቀን ተከበረ
አርትስ 29/02/2011
ቀኑ በአለም ደረጃ ለ 8ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለመጀመሪያ ግዜ ተከብሯል
ሪዲዮሎጂ የአንድን ሠው ጤንነት ወይም ችግር ቁልጭ አድርጎ የሚያሣይ ነው፡፡ የቅዱስ ጳዉሎስ ሚሊኒየምህክምና ኮሌጅ የራዲዮሎጂ ክፍል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ፍትሃ ነገስት ተፈራ ዕለቱን አስመልክተው እንደተናገሩት የቀኑመከበር ዓላማ በዘርፉ ያለውን የመሳሪያውን አስፈላጊነት እና ውድነት እንዲሁም በቅዱስ ጰውሎስ ሚሊኒየም ህክምናኮሌጅ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ለማሳየት ነዉ ብለዋል። በተጨማሪም ከጥቁር አንበሣ ሆስፒታል በመቀጠል በመንግስትሆስፒታል ደረጃ የቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል አገልግሎቱን የሚሰጥ መሆኑን ገልፀው ይኸውም የግል ተቋማትከሚያስከፍሉት ዋጋ ቅናሽ መሆኑን ተናግረዋል ። በመጨረሻም የራዲዮሎጂ ማሽን ከዉጭ በማስገባት በኩል መንግስትአጠናክሮ እንዲሰራበት ጥሪ አስተላልፈዋል።