loading
ግብፅ እንኳን ለራሴ ለዓረብ ጎረቤቶቼ እተርፋለሁ እያለች ነው

ግብፅ እንኳን ለራሴ ለዓረብ ጎረቤቶቼ እተርፋለሁ እያለች ነው

አርትስ 28/02/2011

የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ የአረብ ባህረ ሰላጤ ሀገራት ከየትኛውም ወገን ቀጥተኛ የአደጋ ስጋት  የሚቃጣባቸው ከሆነ  ከሆነ ሀገሬ ሀይሏን ለማንቀሳቀስና ፀብ አጫሪዎችን ለመጋፈጥ ዝግጁ ናት ብለዋል፡፡

አልሲሲ ይህን ያሉት የመዝናኛ ከተማ በሆነችው ሻርም አል ሼክ በወጣቶች ፎረም ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

ፕዝዳንቱ በአረብኛ ለሚተላለፈው ስካይ ኒውስ ሲናገሩ የዓረብ ሀገራት ብሄራዊ ፀጥታ  አደጋ ላይ እንዲወድቅ አንፈቅድም ነው ያሉት፡፡

አልሲሲ በተለይ ኢራንን በስም ጠቅሰው በሌሎች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንደማትገባ ተስፋ እናደርጋለን በማለት በሻርም አል ሼኩ ኮንፈረንስ ላይ የአደጋ ስጋቱ ከየት አቅጣጫ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚካሄደው ትልቅ ለውጥ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ስላለው ግንኙነትም አስታያታቸውን ሰጥተዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡

በኢትዮጵያ ለውጡን ከሚያራምደው አዲሱ አመራር ጋር መልካም ውይይቶቸችን ለማድረግ እንፈልጋለን ያሉት አልሲሲ ዋና ዋናዎቹን የአፍሪካ ችግሮች ግን የአፍሪካ ህብረት ይፈታቸዋል የሚል እምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡ጉዳይ ጣልቃ እንደማትገባ ተስፋ እናደርጋለን በማለት በሻርም አል ሼኩ ኮንፈረንስ ላይ የአደጋ ስጋቱ ከየት አቅጣጫ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚካሄደው ትልቅ ለውጥ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ስላለው ግንኙነትም አስታያታቸውን ሰጥተዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡

በኢትዮጵያ ለውጡን ከሚያራምደው አዲሱ አመራር ጋር መልካም ውይይቶቸችን ለማድረግ እንፈልጋለን ያሉት አልሲሲ ዋና ዋናዎቹን የአፍሪካ ችግሮች ግን የአፍሪካ ህብረት ይፈታቸዋል የሚል እምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *