የትራንስፖርት ባለስልጣን የትራንስፖርት ስምሪት ስራ የኔ ነዉ አለ
አርትስ 27/02/2011
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዳዊት ዘለቀ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት፤ ባለስልጣን መስሪያቤቱ የህብረተሰቡን የትራንስፖርት ችግር ለማቅለል የአጭር እና የረጅም ግዜ ስራዎችን ነድፎ በመስራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከባለስልጣኑ የትራንስፖርት እና የስምሪት ፍቃድ ሳያገኙ አገለግሎቱን የሚሰጡ ተቋማት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ብለዋል፡፡
ኢንጂነሩ በተለይም የአጭር መልዕክትን በመጠቀም እና የስምሪት ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በአዲስ አበባ እና በተለያዩ አካባቢዎች ከባለስልጣን መስሪያቤቱ እውቅና ዉጭ የሚሰሩ ተቋማት ህገወጦች መሆናቸውን ገልጸዋል ፡፡
በተለይም አንዳንዶቹ ተቋማት የንግድ ፍቃዳቸው ከቴክኖሎጂ እና ከዲዛይን ጋር የተያያዙ ስራዎችን እንዲሰሩ የሚፈቅድለቸው ቢሆንም ነገር ግን ፍቃድ ባላገኙበት የትራንስፖርት ስምሪት ላይ እየሰሩ ነዉ ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ኮድ 3 ላልተመዘገበ ዘርፍ አገልገሎት መስጠት ማቆም እንዳለበትም አሳስበዋል።
ባሳለፍነዉ አርብ ሀይብሪድ ዲዛይን የራይድ ቴክኖሎጂ ተቋም በትራንስፖርት ቢሮ ተበድያለሁ ብሎ መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል፡፡