loading
የጀማል ካሾጊ ልጆች የአባታችንን አስከሬን ስጡን እያሉ ነው

የጀማል ካሾጊ ልጆች የአባታችንን አስከሬን ስጡን እያሉ ነው

አርትስ 27/02/2011

 የሟቹ ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ሁለት ወንድ ልጆች የአባታችንን አስከሬን ስጡንና በሃገሩ ሳዑዲ እንቅበረው ፣ እርማችንንም እናውጣ ብለው የሳዑዲ ባለስልጣናትን እየጠየቁ ነው።

በቱርክ የሳዑዲ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ውስጥ እንደተገደለ የተረጋገጠው የካሾጊ  ወንድ ልጆች ሳላህ እና አብዱላሂ ከሲኤንኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ቤተሰቡ ከግድያውም በላይ የአባታቸውን አስከሬን ማግኘት ባለመቻሉ መጽናናት አቅቶታል ብለዋል።

አሟሟቱም በፍጹም የተለመደ አይነት አሟሟት አይደለም። አሁን እኛ የምንፈልገው የአባታችንን አስከሬን ማግኘት እና ከቀረው ቤተሰቡ ጋር ሆነን መዲና ውስጥ በተዘጋጀለት መቃብር ስፍራ በክብር ማኖር ነው ብሏል ሳላህ ካሾጊ።አባታችን በሰላም ማረፉን ማረጋገጥ እንፈልጋለን ብሏል።

ለሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር ጥያቄ ማቅረቡን የሚናገረው ሳላህ በቅርቡ ምላሽ እንደሚሰጡኝም ተስፋ አለኝ ይላል ።

አባታችን የሙስሊም ወንድማማቾች ደጋፊ ነበር የሚባለው ክስ ፍጹም ስህተት ነው ። ሃገሩን የሚወድ ተግባቢ እና ብቃት ያለው ሰው ነበር ብሏል ሳላህ ለሲኤን ኤን በሰጠው አስተያየት።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *