ሩኒ እና ኢብራሂሞቪች በጣም ጠቃሚ ተጫዋች ሽልማት ዝርዝር ውስጥ ተካትተዋል
ሩኒ እና ኢብራሂሞቪች በጣም ጠቃሚ ተጫዋች ሽልማት ዝርዝር ውስጥ ተካትተዋል
አርትስ ስፖርት 22/02/2011
ሁለቱ የቀድሞ ቀያይ ሰይጣኖች በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር በጣም ጠቃሚ ተጫዋቾች ሽልማት (MLS Most Valuable Player Award) ዝርዝር ውስጥ ሊካተቱ የቻሉት ዋይን ሩኒ በዲሲ ዩናይትድ እንዲሁም ዝላታንኢብራሂሞቪች ደግሞ በሎስ አንጀለስ ጋላክሲ በመጀመሪያ የውድድር አመት ቆይታ ባሳዩት አቋም ነው፡፡ ሩኒ ለዲሲ ዩናይትድ በ20 ጨዋታዎች 12 ጎሎችን ሲያስቆጥር ሰባት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ ማቀበል ችሏል፤ቡድኑንም ለሜጀር ሊግ ሶከር ጥሎ ማለፍ ጨዋታ እንዲበቃ አስችሎታል፡፡ ስዊዲናዊው ኢብራሂሞቪች ደግሞ በ27 ጨዋታዎች 22 ጎሎችን ለሎስ አንጀለስ ጋላክሲ ሲያበረክት በ10 ግቦች ላይ ደግሞ ተሳትፎ አድርጓል፡፡ ሁለቱተጫዋቾች በተጨማሪም በውድድር አመቱ ማብቂያ ላይ ለሚካሄደው የሊጉ አዲስ ተጫዋች (እንግዳ) Newcomer of the Year በዕጩ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ሲሆን ኢብራ የአመቱ ኮከብ ተጫዋች ክፍል ውስጥ ተካትቷል፡፡በሜጀር ሊግ ሶከር በጣም ጠቃሚ ተጫዋቾች ሽልማት፤ በዕጩነት ከሁለቱ ተጫዋቾች በተጨማሪ ሚጉዌል አልሚሮን እና ጆሴፍ ማርቲኔዝ ከአትላንታ ዩናይትድ እንዲሁም ካርሎስ ቬላ ከሎስ አንጀለስ እግር ኳስ ክለብ ተካትተዋል፡፡ቢቢሲ