loading
አንድም ተቃዋሚ ፓርቲ መሳሪያ ይዞ ወደኢትዮጵያ አለመግባቱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አረጋገጡ

አንድም ተቃዋሚ ፓርቲ መሳሪያ ይዞ ወደኢትዮጵያ አለመግባቱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አረጋገጡ

አርትስ 22/02/2011

በምዕራብ ወለጋ አካባቢ ላለው አለመረጋጋት ተጠያቂው በስፍራው የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ሃይል መሆኑንም ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአውሮፓ የኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ ጋር በፍራንክፈርት በነበራቸው ውይይት እንደተናገሩት በትጥቅ ትግል ላይ የነበሩና የሰላማዊ ትግል አማራጩን ተቀብለው ወደሃገር ቤት የገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ ትጥቅ አልያዙም።

“ሁሉም ሲገቡ ባንዲራ እያውለበለቡ ነው የገቡት ። መሳሪያው የመጣው ወደሃገር ውስጥ በህገወጥ መንገድ ሲገባ ከኖረ መሳሪያ ላይ ነው” ብለዋል።

በምዕራብ ወለጋ ደንቢዶሎ አካባቢ ለተከሰተው አለመረጋጋት ተጠያቂው በአካባቢው ያሉ በህገወጥ መንገድ የገባ መሳሪያ የታጠቁ ሃይሎች ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኦነግ ሃላፊዎች ሰላማዊ ትግሉን አምነው የገቡ መሆኑንና በምርጫ ማሸነፍም ፍላጎታቸው እንደሆነ ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።

ችግሩ መንግስትም ይሁን ተቃዋሚዎች በሚናገሩት ልክ የሚተገብሩ አለመሆናቸው ነው ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ።

ትጥቅ የፈታው የኦነግ ሃይል ካምፕ ገብቶ ስልጠና በመውሰድ ላይ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒሰትሩ አረጋግጠዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *