loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ የጀርመን ቆይታቸውን ጀመሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ የጀርመን ቆይታቸውን ጀመሩ

የኢፌዴሪ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የፈረንሳይ ጉብኝታቸወን አጠናቀው ጀርመን በርሊን ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

 

በመጀመሪያው የአውሮፓ ጉዞ የጀርመን ቆይታቸውም ከጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ መርክል  ጋር በሁለቱ  አገራት ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ፡፡ ከውይይታቸው ዓበይት ጉዳዮች መካከልየፀጥታ እና ደህንነት እንዲሁም የፀረ ሽብር ጉዳይ አንዱ መሆንን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ተናግረዋል፡፡

የቡድን 20 አባል አገራት የአፍሪካን ልማት ለማገዝ በመሰረቱት ኮምፓክት አፍሪካ በሚሰኘው ጉባኤ ላይም ይገኛሉ፡፡  ኮምፓክት አፍሪካ ለአፍሪካ ልማት የተሻሉ አማራጮችን በመቅረብ ትብብር የማድረግስራ የሚሰራ ሲሆን እስከ አሁን ኢትዮጵያን እና ሰባት የአፍሪካ አገራትን ተጠቃሚ አድርጓል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገራቸው ብዙ ስደተኞችን እንደማስጠለሏ በጀርመን በሚካሔደው ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን የተመለከተው ስብሰባ ላይም እንደሚሳተፉ ታውቋል፡፡

 

ነገ ወደ ፍራንክፈርት በመቅናት “አንድ ሆነን እንስራ ነገን እንገንባ” በሚል መሪ ቃል  ከ 25 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በአካል ተገናኝተው የሚወያዩ ሲሆን በአካል ለማይገኙ በ12 ኤምባሲዎች በኩል የተሰባሰቡ ጥያቄና አስተያየቶችም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይቀርባሉ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የነገው የፍራንክፈርት ውይይት  ቀደም ሲል በሰሜን አሜሪካ ከተካሄደው የቀጠለ ነው፡፡

ኢትዮጵያና ጀርመን ከ 100 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ግንኙነት አላቸው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *