የስሪላንካ ፕሬዚዳንት ሊገድሉኝ አሲረዋል ያሏቸውን የሃገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር አባረሩ
አርትስ 19/02/2011
የፕሬዚዳንቱን ውሳኔ የተቃወሙ ሰዎች ያካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ወደአመጽ በመቀየሩ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ሰዎች መገደላቸውና መቁሰላቸው እየተነገረ ነው።
ፕሬዚዳንት ማይትሪፓላ ሲሪሴና ትናንት ለሃገሪቱ ህዝብ በቴሌቪዠን ቀርበው ባደረጉት ንግግር በርሳቸው እና በቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትሩ ላይ የግድያ ሴራ መታቀዱን መሰረት በማድረግ ለመርማሪዎች ቃሉን የሰጠ አንድ ግለሰብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግድያ ሴራ ውስጥ እንዳሉበት አረጋግጦልናል ብለዋል።
ያለኝ ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ራኒል ዊክረመሲንግን አባርሮ የቀድሞውን ማሂንዳ ራጃፓክሳን በመሾም አዲስ ካቢኔ እንዲያዋቅሩ ማድረግ ብቻ ነው። ለመርማሪዎቹ የደረሰው መረጃ ብዙ ጉዶች ያጨቀ በመሆኑ ይህንን አሁን ይፋ ማድረግም አያስፈልግም ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።
ፕሬዚዳንቱ በግድያ ሴራ ውስጥ አሉበት ያሏቸውን ሌሎች የካቢኔ ሚኒስትሮች ስም ከመግለጽም ተቆጥበዋል።