loading
የጀርመኗ መራሒተ መንግስት ስልጣን በቃኝ አሉ

አርትስ 19/02/2011

ላለፉት አራት ተከታታይ የምርጫ ጊዜያት ጀርመንን በመራሒተ መንግስትነት የመሩት አንጌላ መርኬል በቀጣዩ ምርጫ ላይ የፓርቲያቸው ሊቀመንበር ሆነው መቀጠል  እንደማይፈልጉ አስታወቁ።

 

መርኬል ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በወግአጥባቂ ክርስቲያን ዴሞክራትስ ፓርቲ ሊቀመንበርነት ላለፉት 18 ዓመታት ያገለገሉበት እና በመራሂተ መንግስትነት ለ13 ዓመታት ጀርመንን የመሩበት ዘመን እዚህ ዙር ላይ ያበቃል።

 

የ64 ዓመቷ መራሂተ መንግስት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት ፓርቲያቸው በሁለተኛው ሃገራዊ ምርጫ እድል ፊቷን ካዞረችበት በኋላ ነው።

 

የአንጌላ መርክል ውሳኔ ብዙዎችን ቢያስገርምም ግለሰቧ የአውሮፓን ፖለቲካ ላለፉት 13 ዓመታት ተቆጣጥረው የቆዩ ጠንካራ ሴት በመሆናቸው ግን የሚወስኑትን ጉዳይ በሚገባ የሚያውቁ ናቸው ተብሎላቸዋል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *