ታላቁን ቤተ መንግሥት ወደ ሙዚየምነት ለመቀየር የፈረንሣይ መንግሥት ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባ
ታላቁን ቤተ መንግሥት ወደ ሙዚየምነት ለመቀየር የፈረንሣይ መንግሥት ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባ
አርትስ 19/02/2011
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤትና መኖሪያ የሚገኝበትን የአፄ ምኒልክ ቤተ መንግሥት በዘመናዊ መንገድ በማደስና በማልማት ወደ ሙዚየምነት ለመቀየር፣ የፈረንሣይመንግሥት ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱ ታውቋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶር) ሐሳብ አመንጪነት ታላቁን የምኒልክ ቤተ መንግሥት በማደስና ተጨማሪ ልማቶችን በማከናወን፣ ለሕዝብና ለጎብኝዎች ክፍትየሚሆን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ዕቅድ ተይዟል፡፡
ይህንንም በፍጥነት በተግባር ለመቀየር የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ሚኒስቴር ኃላፊነት ተሰጥቶታል።
ፕሮጀክቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸው በበላይነት እየተከታተሉት እንደሚገኙም ታውቋል። በዚህም መሠረት የተለያዩ አገሮች ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኝነታቸውን እንዳሳዩ፣በዋናነት ግን የፈረንሣይ መንግሥት አስፈላጊውን የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱን ሪፖርተር ዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግንቦት ወር 2010 ዓ.ም. በውጤታማ ሥራ አፈጻጸም ላይ በወቅቱ ለነበሩ የካቢኔ ሚኒስትሮች ባደረጉት ገለጻ፣ የአፄ ምኒልክ ቤተ መንግሥትን የቱሪዝምመዳረሻ ማድረግ እንደሚገባ መግለጻቸው ይታወሳል።