loading
አሜሪካ ሳዑዲ አረቢያ ላይ እገዳ ልትጥል እንደምትችል ፍንጭ ሰጠች

አርትስ 14/02/2011

 አነጋጋሪ በሆነው የጋዜጠኛ ጀማል ካሹጊ ጉዳይ ሳዑዲ የሰጠችውን ምላሽ አሜሪካ  አስነዋሪ ስትል  በተደጋጋሚ እያወገዘች ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከዎል ሰትሪት ጆርናል ጋር ባደረጉት ቆይታ በጋዜጠኛው ግድያ ላይ የሳውዲ  የቀድሞ ነገስታት እጃችው እንዳለበት እንደሚጠረጥሩ ተናግረው የአሁኑ የሳውዲ ንጉስ ልዑል ሳልማን ስለ ወንጀሉ ብዙም መረጃ ያላቸው አይመስለኝም ብለዋል፡፡

ትራምፕ የትኛውም አካል ቢያቀናብረው ያ አካል ከባድ ችግር ውስጥ እንደገባ ማወቅ አለበት እያሉ ነው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዎ በበኩላቸው አሜሪካ ተጠያቂ የሆኑ ሰዎችን ለመቅጣት የቪዛ እገዳ ጭምር ልትተገብር እንደምትችል አሳውቀዋል፡፡ በተጨማሪም ማዕቀብ እስከመጣል የሚደርስ እርምጀ እንወስዳለን በማለት ደጋግመው አስጠንቅቀዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *