loading
አሜሪካ በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያለውን ለውጥ ትደግፋለች

አርትስ 14/02/2011

አሜሪካ በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያለውን ለውጥ እንደምትደግፍ አምባሳደር ሚካኤል ሬይነር አስታወቁ።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ለጋዜጠኞች ባዘጋጀው መድረክ ላይ አምባሳደር ሬይነር እንደተናገሩት አዲሱ የኢትዮጵያ አመራር ከአሜሪካ ጋ ተባብሮ ለመስራት ፍላጎት ያለው መሆኑን አረጋግጦልናል ብለዋል።

በተመሳሳይም የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስተዳደር በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለማስፈን የሚያደርገውን ጥረት አሜሪካ ትደግፋለች ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አንዳንድ ሰፍራዎች እየታየ ያለውን ግጭት እና ጥፋት በዴሞክራሲ ሂደት የሚያጋጥም መሰናክል ነው ብለውታል አምባሳደሩ።

ኤምባሲያቸው ከኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በሰብዓዊ መብት አጠባበቅ፣ በመልካም አስተዳደር እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ላይ አንድ ቀን የፈጀ ውይይት ማካሄዱን አምባሳደሩ ጠቁመዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *