loading
የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ከማዘጋጃ ቤት እንዲወጣ ተወሰነ

አርትስ 14/02/2011

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ከማዘጋጃ ቤት ቅጥር ግቢ እንዲወጣ ተወስኗል፡፡

ቢሮው ለዓመታት ከነበረበት ማዘጋጃ ቤት እንዲወጣ የተወሰነው፣ በማዕከል ደረጃ የሚገኙ ሁሉም የመሬት ተቋማት በአንድ ላይ ሆነው አገልግሎት መስጠት አለባቸው ተብሎ ነው፡፡

በዚህ መሠረት የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮና በሥሩ የሚገኙ ስድስት ተቋማት፣ እንዲሁም የፕላን ኮሚሽንና የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ካሉበት ተነስተው ቦሌክፍለ ከተማ አካባቢ ይዛወራሉ ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ ኢኒጂነር ሽመልስ እሸቱ  እንደገለጹት፣ የመሬት ተቋማት ተበታትነው ከሚሰጡት አገልግሎት ይልቅ በአንድ ቦታሆነው የሚሰጡት አገልግሎት የተሻለ መሆኑ ታምኖበታል ።

በዚህ መሠረት ሁሉም የመሬት ተቋማት አንድ ላይ ሆነው አገልግሎት መስጠት የሚጀምሩበት አሠራር  ተዘርግቷል ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *