የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ሶስተኛ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ምሽት ይካሄዳሉ፡፡
አርትስ ስፖርት 13/02/2011
ዛሬ ምሽት ከምድብ አምስት እስከ ስምንት የሚገኙ ቡድኖች ጨዋታዎቻቸውን የሚያካዱ ሲሆን በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ይከናወናሉ፡፡ በዚህም ምድብ አምስት ላይ ምሽት1፡55 ሲል ባየር ሙኒክ ወደ ግሪክ አቅንቶ ከ ኤኢኬ አቴንስ ጋር ሲጫወት፤ ምሽት 4፡00 ሲል አያክስ በሜዳው ቤኔፊካን ያስተናግዳል፡፡ ምድቡን አያክስ እና ሙኒክ በእኩል አራትነጥብ ይመሩታል፡፡ ምድብ ስድስት ላይ የእንግሊዙ ማንችስተር ሲቲ ከዩክሬኑ ሻክታር ዶኔስክ እንዲሁም ሆፈንየም ከሊዮን በተመሳሳይ ምሽት 4፡00 ይጫወታሉ፡፡ ምድቡን ሊዮንበአራት ነጥብ፤ ማ.ሲቲ በሶስት ነጥብ ይመሩታል፡፡ በሰባተኛው ምድብ ደግሞ ሪያል ማድሪድ በሜዳው ሳንቲያጎ ቤርናባው ቪክቶርያ ፕለዘንን ሲያስተናግድ፤ ከምድቡ ሮማ በሮምኦሎምፒክ ሲኤስኬኤ ሞስኮን ይገጥማል፤ ጨዋታዎቹ በተመሳሳይ ምሽት 4፡00 ላይ ይካሄዳሉ፡፡ የሞስኮው ቡድን በአራት ነጥቦች ምድቡን ሲመራ ማድሪድና ሮማ በሶስት ነጥቦችይከተላሉ፡፡ በመጨረሻው ምድብ ሰምንት ላይ በግዙፉ ኦልድትራፎርድ ስታዲየም በጉጉት በሚጠበቀው ፍልሚያ፤ ምሽት 4፡00 ስዓት ላይ ማንችስተር ዩናይትድ የጣሊያኑን ዩቬንቱስያስተናግዳል፤ በዚህ ጨዋታ ሮናልዶ እና ፖግባ የቀድሞ ክለቦቻቸውን በተቃራኒ ማሊያ ይገጥማሉ፡፡ እዚሁ ምድብ አስቀድሞ ምሽት 1፡55 ሲል ያንግ ቦይስ ከቫሌንሲያ ይጫዋታሉ፡፡ዩቬንቱስ በስድስት ነጥብ ሲመራ ዩናይትድ በአራት ነጥብ ይከተላል፡፡