loading
የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ የድርጅቱን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ከ11 ወደ 9 ዝቅ አደረገ

አርትስ 09/02/2011
ማዕከላዊ ኮሚቴው ትናንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ነው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥሩን ቀደም ሲል ወደነበረበት የቀነሰው።
በድርጅቱ ህገደንብ መሰረት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥርን የመጨመርም ሆነ የመቀነስ ስልጣን የድርጅታዊ ጉባኤ ነው።
ቀደም ሲል ማዕከላዊ ኮሚቴው ከዘጠኝ ወደ 11 ቁጥሩን ከፍ ሲያደርግ በድርጅታዊ ጉባኤ ውሳኔ አለመሆኑም የማስተካከያ ውሳኔው መነሻ እንደሆነ ተመልክቷል።
ድርጅቱ በቅርቡ ባካሄደው ድርጅታዊ ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መምረጡ ይታወሳል።
በምርጫው መሰረትም፦
1. ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል
2. ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር
3. አቶ ጌታቸው ረዳ
4. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ
5. ዶክተር አብረሃም ተከስተ
6. ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም
7. አቶ ጌታቸው አሰፋ
8. ዶክተር አምባሳደር አዲስዓለም ባሌማ
9. አቶ ዓለም ገብረዋህድ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል፡፡ FBC

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *