loading
የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፒ ኮንቴ አዲስ አበባ ገቡ

አርትስ 01/02/2011
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ባደረጉላቸው ጥሪ መሰረት ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ወደ አገራችን የመጡት ጁሴፒ ኮንቴ በአገራችን በሚኖራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ ታውቋል::
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፣ ሚኒስትሮች እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኙ የኢጣሊያን ማህበረሰብ አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ይህም ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በቀጣይ የዲፕሎማሲ ግኑኝነታቸውን ከአውሮፓ አገሮች ጋር ለማጠናከር ማቀዳቸውን ተከትሎ የሚከናወን ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ተብሏል::
ጠቅላይ ሚኒስትር ኮንቴ ለክብራቸው መድፍ ተተኩሶላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ ዶ/ር አብይ አህመድ በተጨማሪ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ክዌሲ ኳርቴይ ጋር እንደሚገናኙም ይጠበቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኮንቴ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን እንዳጠናቀቁ በኤርትራ ጉብኝት እንደሚያደርጉም ይጠበቃል፡፡
ኢትዮጵያና ጣሊያን ከ100 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሁለገብ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው፡ ፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *