loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በሞተር የሚንቀሳቀስ ተሽከርካሪ ወንበር አበረከቱ

አርትስ 17/01/2011

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ ነው በሞተር የሚንቀሳቀስ ተሽከርካሪ ወንበር ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ስጦታ ያበረከቱላቸው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ኃላፊ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገጻቸው እንደገለፁት ስጦታውንም ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አስረክበዋል።

ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ የመኖሪያ ቤት ቁልፍ አስረክበዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *