loading
ትራምፕ በሀገሬ የመጣ በዓይኔ መጣ እያሉ ነው

አርትስ 05/13/2010
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይ ሲሲ) ዳኞች ላይ ማዕቀብ እንደሚጥሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው ትራምፕ ማዕቀቡን እጥላለሁ ያሉት ፍርድ ቤቱ አሜሪካ በአፍጋኒስታን የጦር ወንጀል ፈጽማለች የሚለውን ጥርጣሬ ይዞ ምርመራውን የሚቀጥል ከሆነ ነው፡፡
እንዲሁም ፍልስጤም አይ.ሲ.ሲ በእስራኤል ላይ የሚያደርገውን ምርመራ እንዲያፋጥን የምታደርገውን ግፊት የማታቆም ከሆነ ዋሽንግተን የሚገኘውን የፍልስጤም የነጻነት ድርጅት ቢሮ እንዘጋለን የሚል ማስፈራሪያም ከነጩ ቤተ መንግስት እየተሰማ ነው፡፡
የትራምፕ ብሄራዊ የደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን ሀገራችን ዜጎቿ ብቻ ሳይሆኑ የአጋሮቿም ፍትህ ሲጓደልባቸው ዝም ብላ አታይም በማለት ለእስራኤልም ጭምር ያላቸውን ተቆርቋሪነት አሳይተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *