loading
ኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ዘርፏን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት አደረገች ::

አርትስ 30/12/2010

ኢትዮጵያ በሎጂስቲክ ዘርፉ ላይ የውጭ ባለሃብቶች እንዳይሳተፉ የሚከለክለውን ደንብ ማንሳቷን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ አስታወቀ፡፡
ኢቢሲ በደረገፁ እንደገለፀው ቦርዱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የሎጂስቲክ ዘርፉን ቀልጣፋ ፤ በሙያ የተደገፈና ዘመናዊ አሰራሮችን እንዲከተል ለማስቻል እንደሆነ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መኮንን ሃይሉ ተናግረዋል፡፡
በሂደቱም የውጭ ካፒታልና ሙያተኞች በቀጥታ ስለሚሳተፉ ሃገሪቱ ተጠቃሚ ትሆናለች ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት መሰረቱን በኤክስፖርት ላይ ባደረገው በማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ በርካታ ግዙፍ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ ላይ እንደመገኘቷ መጠን የሎጂስቲክ ዘርፉ ውጤታማና ፈጣን መሆን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ይህም ሃገሪቱ ከማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለማግኘት ያቀደችውን ገቢ ከማሳካት ረገድ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ነው አቶ መኮንን ሃይሉ ያብራሩት፡፡
በሎጂስቲክ ዘርፉ ላይ የውጭ ባለሃብቶ እንዲሳተፉ መደረጉ መንግስት የሃገሪቱን ምጣኔ ሃብት ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ለማድረግ ያቀደው አካል እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *