loading
6ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ፤ የህዳሴዉ ግድብ እና ግብጽ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2013 ምርጫዉን ሰላማዊ በማድረግ በህዳሴዉ ግድብ መጓተት እና በሀገር ሰላም ላይ ሊደርስ የሚችልን ጉዳት ከወዲሁ ልንከላከል ይገባል ተባለ፡፡ አርትስ ያነጋገራቸዉ በሀዳሴ ግድቡ እና በአባይ ወንዝ ላይ የሚሰሩ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ፤ግብጽ ምርጫዉን ሰላማዊ ማድረግ ካልቻልን እንደ ወርቃማ አድል ተጠቅማበት ፤ግድቡ እንዲዘገይ ልትጠቀምብት እንደምትችል ከዚህ በፊት ፍንጭ ማሳየትዋ ገልጸዋል፡፡

በሀዳሴ ግድቡ እና በአባይ ወንዝ ላይ የሚሰሩ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎቹ ጋዜጠኛ ሰላም ሙልጌታና የአባይ ፖለቲካና የባዕዳን ተልዕኮ መጽሀፍ ደራሲ ጋዜጠኛ ስላባት ማናዬ ይህ የግብጽ ፍላጎት በኮቪድ 19 ምክንያት ምርጫ በመራዘሙ ለግዜዉ ባይሳካም በዘነድሮ ምርጫ ማንኛዉንም ከምርጫ ጋር የተያያዘ የሚፈጠሩ ችግሮች ካሉ ያንን ለማባባስ እንደምትስራ መገመት አያዳግትም ብለዋል::

ግብጽ የህዳሴ ግደቡን ግንባታ ለማደናቀፍ አሁን በየቦታዉ ያሉ ግጭቶችንም ከምርጫዉ በተጨማሪ ልትጠቀምብት ትችላልች ያሉት ባለሞያዎቹ ፤ መንግስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢትጵያዉ ያን የሚያጋጥሙ ችግሮችን ብልህ በመሆን ምንፈታበት ግዜ አሁን ነዉ ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *