loading
51 ሺህ 89 ኢትዮጵያዊያን ከሀገር ወጥተው የት እንዳሉ አይታወቅም::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣2013 ከሀገር ውጪ ፈልሰው አድራሻቸው ያልታወቁ 51 ሺ 89 ዜጎች መኖራቸውን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ኤጀንሲው የአለማቀፍ ፍልሰት ድርጅት እና ዳኒሽ ከተባለ ግብርሰናይ ድርጅት ጋር በመተበባር ባስጠናው ጥናት 51 ሺ 89 ኢትዮጵያዊያን ከሀገር እንደወጡ የት እንዳሉ እንዳልታወቀ ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡ ከ41 ሺህ በላይ ቤተሰቦች ለተካተቱበት ለዚህ ጥናት የኢትዮጵያ መንግስት 36 ሚሊዮን ብር ያወጣበት ሲሆን አይ. ኦ .ኤም ደግሞ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን የማዕከላዊ
ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አሳልፈው አበራ ተናግረዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስን ሁኔታ በተመለከተ ጥናት ከተደረገባቸው ቤተሰቦች ውስጥ 40 በመቶ ያህሉ በኮቪድ- 19 ምክንያት የዕለት ገቢያቸው የቀነሰ እና ሥራቸውን የለቀቁ መሆናቸው ተመላክቷል። በጥናቱ ገለጻም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሰው ኃይል ምጣኔ 65 በመቶ ሲሆን፤ ለሥራ ዝግጁ የሆኑት ደግሞ 27 በመቶ ናቸው ተብሏል።በተጨማሪም 8 በመቶ ያህሉ ሥራ አጥ መሆናቸው ተገልጿል። በተጨማሪም የወጣቱ የሥራ አጥነት ምጣኔ በከፍተኛ ደረጃ በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ተመዝግቧል።

በከተማና በገጠር የሥራ አጥነት ምጣኔ ሲነጻጸርም የከተማ  ዜጎች ሥራ በማጣት በእጥፍ ልዩነት አሳይተዋል። የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ተሾመ አድኖ የገጠሩ ወጣት ቁርጥራጭ መሬቶች ስላነሱት በሌላ አማራጭ ወደ ሥራ የመሠማራትና ሥራ የመፍጠር ዕድሉ ከከተማው ጋር ሲነጻጸር የተሻለ መሆኑን ተናግረዋል። ጥናቱ ሰፋ ያለ ጊዜ የወሰደ ሲሆን፤ የተጠቀሙት መረጃ እና ያሳተፉት የማህበረሰብ ክፍል አብዛኛውን ማህበረሰብ የሚወክል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የተደረጉት ዳሰሳም አመርቂ መሆኑ ተነግሯል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *