33 ሺ 250 የአሜሪካ ዶላርና 6 ሺ 500 የሳውዲ ሪያል በቦሌ ኤርፖርት በኩል ወደ ዱባይ ሊወጣ ሲል ተያዘ
33 ሺ 250 የአሜሪካ ዶላርና 6 ሺ 500 የሳውዲ ሪያል በቦሌ ኤርፖርት በኩል ወደ ዱባይ ሊወጣ ሲል ተያዘ
አርትስ19/04/2011
በቦሌ ኤርፖርት በኩል አድርጎ ወደ ዱባይ ሊወጣ የነበረ 33 ሺ 250 የአሜሪካ ዶላርና 6 ሺ 500 የሳውዲ ሪያል በአልሙኒየም ወረቀት ተጠቅልሎ ሊወጣ ሲል ትናንት ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ በጉምሩክ ሰራተኞች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን በገቢዎች ሚኒስቴር የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ህገ ወጥ ገንዘቡን ይዛ ስትንቀሳቀስ የነበረቸው ተጠርጣሪ መቅደስ ጽጌ የተባለችው መንገደኛ በቁጥጥር ስር ውላ አስፈላጊው የማጣራት ስራም እየተሰራ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
በተመሳሳይ ዜና ታህሳስ 10/2011 ዓ.ም በጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት 41 ሺ 693 የአሜሪካ ዶላር በህገወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል፡፡
ከገቢዎች ሚኒስቴር እንዳገኘነዉ መረጃ መሰል ህገ ወጥ ድርጊትን ለመከላከል ኮሚሽኑ ከምንጊዜውም በላይ ጠንክሮ እየሠራ እንደሚገኝ ገልጾ፤ህብረተሰቡ ይህንን መሰል ድርጊት ሲመለከት ለኮሚሽኑ ጥቆማ በማቅረብ ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል፡፡