loading
የዋጋ ጭማሬ የታየበት የበዓል ግብይት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 የዘንድሮው የበዓል ግብይት በሁሉም መልኩ የዋጋ ጭማሬ የታየበት መሆኑን ሸማቾች ተናገሩ። የፋሲካ በዓልን በማስመልከት በተለያዩ አካባቢዎች በተዘጋጁ ኤግዚቢሽኖች፣ የበሬ፣ የበግና ፍየል፣ የዶሮ ግብይት ስፍራዎች የዋጋ ንረት ታይቷል፡፡ ለአብነትም የበሬ ዋጋ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከ10 እስከ 15 ሺህ ብር ጭማሪ ማሳየቱ ነው የተገለፀው፡፡  ለበሬ ዋጋ መጨመር በማጓጓዝ ሂደት የነዳጅ ዋጋ […]

ኤች አር 6600” እና “ኤስ 3199” ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰልፍ በኒው ጀርሲ ግዛት ተካሄደ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 ኤች አር 6600” እና “ኤስ 3199” ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰልፍ በኒው ጀርሲ ግዛት ተካሄደ:: በትናትናው ዕለት በ “ኤስ 3199” ረቂቅ ሕግ አርቃቂ ሴናተር ሮበርት ሜኔንዴዝ (ኒው ጀርሲ) ቢሮ ፊት ለፊት በተከናወነው ሰልፍ ላይ “ረቂቅ ሕጎቹ ኢትዮጵያንና ኤርትራን የሚጎዱ ናቸው”፣ ”ማዕቀብ ይገድላል ማዕቀብ ምንም አይጠቅምም”፣ “ኤች አር 6600” እና “ኤስ 3199” […]

የእስራኤል ተዋጊ ጄቶች በጋዛ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ተነገረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 የእስራኤል ተዋጊ ጄቶች በጋዛ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ተነገረ፡፡ እስራኤል በዚህ ሳምንት ለሁለተኛ ጊዜ በማእከላዊ ጋዛ ሰርጥ የአየር ጥቃት መፈፀሟ ተነግሯል፡፡ አልጄዚራ የዐይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው የእስራኤል ተዋጊ ጄቶች የሮኬት ሞተሮችን ከሚያመርተው እና ከመሬት በታች በሚገኘው ህንፃ ላይ ጥቃት አድርሰዋል። የመረጃ ምንጩ ይሄንን ዘገባ እስካጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በጥቃቶቹ በማዕከላዊ ጋዛ በሚገኘው […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለጎዳና ተዳዳሪዎችና አቅመ ደካሞች በቤተ-መንግሥት ማዕድ አጋሩ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለጎዳና ተዳዳሪዎችና አቅመ ደካሞች በቤተ-መንግሥት ማዕድ አጋሩ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ጧሪ ለሌላቸው አረጋዊያን፣ የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ በተለያዩ ምክንያቶች ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ህፃናትና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው በድምሩ 230 ወገኖች ማዕድ አጋርተዋል።በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት ወገኖች በቤተ-መንግሥት ተገኝተን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተደረገልን ግብዣና መልካም መስተንግዶ እናመሰግናለን ብለዋል። ማዕድ ተጋሪዎቹ […]

የጥቁር አንበሳ የልብ ሕክምና ማዕከል የማስፋፊያ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቆ ሥራ ጀመረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2014 የጥቁር አንበሳ የልብ ሕክምና ማዕከል የማስፋፊያ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቆ ሥራ ጀመረ፡፡ በዛሬው ዕለት የተመረቀው የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ የተለያዩ የሕክምና ግብዓቶች እንደተሟሉለት ተነግሯል። ለአብነትም በአፍሪካ ብቸኛው ልብ ሳይከፈት ቀዶ ህክምና ማድረግ የሚያስችል መሣሪያ ተበርክቶለታል ተብሏል፡፡ በአጠቃላይ ለፕሮጀክቱ 39 ነጥብ 720 ሚሊየን ዶላር ወጪ የሚደረግበት ሲሆን ወጪውም 50 በመቶው በኔዘርላንድስ መንግሥት […]

ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይፋ አደረገ።

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2014 ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይፋ አደረገ። የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎችምደባ ማድረጉን ሚኒስቴሩ ገልጿል። ከዚህ በፊት በተገለጸዉ የመቁረጫ ነጥብ ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋርና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተጨማሪ ተማሪዎች ምደባ […]

ተሸከርካሪን በመጠቀም የሚፈፀም የቅሚያ ወንጀል ‹‹ሿሿ›› መበራከት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 በአዲስ አበባ የሌብነት ወንጀል በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን ፖሊስ አስታወቀ:: በአዲስ አበባ ለህዝብ ስጋት ከሆኑ ከባድ ወንጀሎች መካከል በተለያየ መንገድ የሚፈፀም የሌብነት ወንጀል በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ተናግረዋል። ከእነዚህ ከባድ ወንጀሎች ውስጥ ተሸከርካሪ በመጠቀም የሚፈፀም የቅሚያ ወንጀል፣ በተለምዶ ‹‹ሿሿ›› የሚባለው መኪና ውስጥ የሚፈፀም […]

የወባ በሽታን ከሀገሪቱ ለማጥፋት ህብረተሰቡ የወባ ማስወገድ አፈጻጸም መመሪያዎችንና መከላከያ ዘዴዎችን በአግባቡ ሊተገብር እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 የወባ በሽታን ከሀገሪቱ ለማጥፋት ህብረተሰቡ የወባ ማስወገድ አፈጻጸም መመሪያዎችንና መከላከያ ዘዴዎችን በአግባቡ ሊተገብር እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡ የወባ ቀንን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ 75 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ መልክዐ ምድር ለወባ በሽታ ስርጭት አመቺ መሆኑን ጠቅሰዋል። 52 በመቶ የሚሆነው የሀገሪቱ ህዝብ በእነዚህ አካባቢዎች እንደሚኖር ተናግረዋል። በወባ […]

ሩሲያ ዩክሬን ላይ የኒውክሌር ግጭት ሊቀሰቀስ እንደሚችል አስጠነቀቀች::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 ሩሲያ ዩክሬን ላይ የኒውክሌር ግጭት ሊቀሰቀስ እንደሚችል አስጠነቀቀች:: ሞስኮ ባወጣችው መግለጫ ኔቶ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ በማቀበል የእጅ አዙር ጦርነት ከፍቶብኛል ስትል ወቀሳ ሰንዝራለች፡፡ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቨሮቭ ከአንድ የሀገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ መላው ዓለም ይህን ጉዳይ አቅልሎ መመልከት የለበትም ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ የላቭሮቭ ቃለ መጠይቅ የተሰራጨው […]

በንጹሃን ሕይወትና ንብረት ላይ የሚደርስን ጥፋት አንታገስም-የአማራ ክልል::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 20 ፣ 2014 በጎንደር ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአማራ ክልል አስታወቀ፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀሰው ዕለተ ማክስኞ ሲሆን ክልሉ በሰጠው መግለጫ የጸቡ ምክንያት ሃይማኖታዊ ሽፋን ያለው መሆኑን አብራርቷል፡፡ ሼህ ከማል ለጋስ የተባሉ ግለሰብ ህይወት ማለፍን ተከትሎ የቀብር ስነ ስርዓት በሚፈጸምበት ወቅት በአቅራቢያው በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ለቀብር የሚሆን ድንጋይ […]