loading
በባንኮች ላይ እተፈጸመ ያለው የማጭበርበር ወንጀል አሳሳቢ ሆኗል-ፍትህ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 ፍትህ ሚኒስቴር በጥናት ደረስኩበት ያለውን በባንኮች ላይ የተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ይፋ አደረገ፡፡ ሚኒስቴሩ በጉዳዩ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት በባንኮች ላይ ከ370 ቢሊዮን ብር በላይ የማጭበርበር ወንጀል ሙከራ ተደርጓል ብሏል። በዚህም በተለያዩ ባንኮች ከ1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ምዝበራ እንደተፈጸመባቸው ነው የተነገረው፡፡ […]

በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመረቀ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመረቀ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የተመረቀው ማዕከሉ ቀድሞ በሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎች ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በአምስት እጥፍ እንደሚያሳድገው ተነግሯል፡፡ ይህም ለኩላሊት ህመምተኞች እፎይታን ይሰጣል ተብሎ ተስፋ እንደተጣለበት ከከንቲባ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማዕከሉን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ባዩት […]

ውስጣዊና የውጭ ጫና የበረከተባት ሱዳን የጣለችውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳች፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 ውስጣዊና የውጭ ጫና የበረከተባት ሱዳን የጣለችውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳች፡፡ ወታደራዊ አስተዳደሩን የሚመሩት ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ከወራት በፊት ተጥሎ የነበረው የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ መነሳቱን ይፋ ሲያደርጉ ከአዋጁ ጋር በተገናኘ የታሰሩ ሰዎች እደሚፈቱም ፍንጭሰጥተዋል ተብሏል፡፡ የአዋጁ መነሳት የተሰማው በሱዳን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ በሳምንቱ መጨረሻ ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች ባፀጥታ ሃይሎች መገደላቸው […]