loading
የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ለአሽከርካሪዎች የሰጠው ማስጠንቀቂያ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2014 የትራንስፖርት አገልግሎቱን በሚያስተጓጉሉ የህዝብ ትራንስፖርት ሰጪ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ አስጠነቀቀ::የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር እጸገነት አበበ ለኢቢሲ እንደገለጹት፣ ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች፣ ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት ድጋፍ ሰጪዎችን ጨምሮ በተመደቡበት የስምሪት መስመር በመገኘት በተቀመጠው የታሪፍ መጠን ብቻ አገልግሎቱን መስጠት ይገባቸዋል፡፡ በጥናት መመለስ […]

አንዲት በጎ አድራጊ ግለሰብ ለዘውዲቱ ሆስፒታል ዘመናዊ የአምቡላንስ ድጋፍ አደረጉ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2014 አንዲት በጎ አድራጊ ግለሰብ ለዘውዲቱ ሆስፒታል ዘመናዊ የአምቡላንስ ድጋፍ አደረጉ፡፡ የዘውዲቱ ሆስፒታል ፋርማሲስት የሆኑት ወይዘሮ ሃና ልካስ ለሆስፒታሉ ያደረጉት የአምቡላንሶ ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ሲሆን፥ በተለይ በእርግዝና ላይ ያሉ እናቶች አስፈላጊውን የህክምና ድጋፍ እያገኙ ወደ ሆስፒታል እንዲደርሱ እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡ አምቡላንሱ ዘመናዊ የመተንፈሻ ቬንትሌተር የተገጠመለት ሲሆን፤በተለይ እናቶች […]

በደቡብ ሱዳን የኮሌራ በሽታ መከሰቱ በደቡብ ሱዳን በተከሰተው የኮሌራ በሽታ አንድ ሰው ሲሞት 31 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ታውቋል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2014 በደቡብ ሱዳን የኮሌራ በሽታ መከሰቱ በደቡብ ሱዳን በተከሰተው የኮሌራ በሽታ አንድ ሰው ሲሞት 31 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ታውቋል ተባለ፡፡ የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2017 ወዲህ በደቡብ ሱዳን የኮሌራ በሽታ ሲከሰት ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡ በሽታው የተከሰተው በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው ዩኒቲ ግዛት ሩቦንካ ካውንቲ ሲሆን በበሽታው […]