loading
መንግሥት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2014 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙ እና ለመሳተፍ ፍላጎት ካላቸው የህንድ ባለሀብቶች እና ከህንድ የኢንቨስትመንት ፎረም አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡ አምባሳደር ሬድዋን ኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከአሁን በፊት ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ያልሆኑ የኢንቨስትመንት ዘርፎችን ጭምር ክፍት ማድረጓን አስታውሰዋል። የሕንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ […]

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ ማካሄድ ጀመረ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2014 የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጣሂር መሐመድ ያለፉት ጊዜያት የፓርቲው እንቅስቃሴ እንደሚዳሰስና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችም እንደሚቀመጡ አስታውቀዋል። የማዕከላዊ ኮሚቴው ስብሰባ በወቅታዊው የፖለቲካ ሁኔታ አብን ለሕዝቡ ሊያበረክት ስለሚችለው አስተዋጽኦ፣ በቅርቡ በሚደረገው የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባዔ ቅድመ ዝግጅት ላይ፣ ስድስተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ምን ይመስል እንደነበርና በሂደቱ የአብን ሚና ምን እንደነበር በስፋት […]

ኢራን በሰሜናዊ ኢራቅ በሚገኝ የእስራኤል ጦር ሰፈር ላይ የድሮን ድብደባ ማደረሷ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2014 ቴህራን ይህን እርምጃ የወሰደችው ባለፈው ወር የእስራኤል አየር ሃይል በአንድ የድሮን ፋብሪካዋ ላይ የፈጸመውን ጥቃት ለመበቀል ነው ተብሏል፡፡ እስራኤል ጥቀት ፈጸመችበት የተባለው ፋብሪካ የኢራን ሁነኛ የወታደራዊ ድሮኖች ማምረቻና ማከማቻ መሆኑ ነው የተሰማው፡፡ ይሁን እንጂ እስራኤል እስካሁን በጉዳዩ ዙሪያ ማስተባበያም ይሁን ድርጊቱን ስለመፈፀሟ አንዳችም መግለጫ አልሰጠችም፡፡ ደረሰ የተባለው ጥቃትም […]