loading
የፖሊስ ልዩ የበዓል ዝግጅት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2013 የስቅለት እና የትንሳኤ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ወቅቱን ያገናዘበ የፀጥታ ዕቅድ አውጥቶ ወደ ተግባር መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡በበዓላት መዳረሻ ወቅቶች ከወትሮው በተለየ ጨምሮ የሚታየውን የሰዎች እና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተከትሎ የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰት እና በተለይም በግብይት፣ በመዝናኛ ሰፍራዎች እና በዕምነት ተቋማት አካባቢ ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ ከወትሮው የተለየ ዝግጅት በማድረግ የፀጥታ […]

ለህግ ታራሚዎች የተደረገ ይቅርታ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22 ፣ 2013የአማራ ክልል ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን ገለጸ የአማራ ክልላዊ መንግስት ለ2ሺህ 705 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል፡፡ የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አለምሸት ምህረቴ ለኢዜአ እንደገለጹት የክልሉ መንግስት ለታራሚዎቹ ይቅርታ ያደረገው በይቅርታ ቦርዱ ተመርምሮ መስፈርቱን አሟልተው በመገኘታቸው ነው። የይቅርታው […]

ህዝቡ በዓብይ ፆሙ ለሀገር ሠላም ተግቶ ሲፀልይ የነበረውን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22 ፣ 2013የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ርስቱ ይርዳው ህዝቡ በፆም ወቅት ያሳየውን መተዛዘን፣ መከባበርና ለሀገር ሠላምና ደህንነት ተግቶ ሲፀልይ የነበረውን በጎ ተግባር ከፆሙፍቺ በኋላም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። በክልሉ የትንስዔ በዓልን በማስመልከት ለ970 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታና የእስራት ቅነሳ መደረጉን የገለፁት አቶ ርስቱ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል። ምክትል […]

የአሚሶም ሽልማት ለኢትዮጵያ ወታደሮች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2013 አሚሶም ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት አስተዋጽኦ ላበረከቱ የኢትዮጵያ ወታደሮች የክብር ሜዳልያ ሸለመ:: በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል (አሚሶም) ስር የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆኑ፡፡ ሽልማቱ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች በሶማሊያ በነበራቸው የአንድ አመት ከስድስት ወር ቆይታ በሃገሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በተደረገው ጥረት ላደረጉት […]

በአዲስ አበባ አንድ ግለሰብ ስጋ አንቆት ሕይወቱ አለፈ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2013 በአዲስ አበባ አንድ ግለሰብ ስጋ አንቆት ሕይወቱ አለፈ፡፡ በፋሲካ በአል ቀን ስጋ እየተመገበ የነበረው ወጣት ስጋው አንቆት ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡ ድንገተኛ የሞት አደጋው የደረሰው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ካዲስኮ አካባቢ እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጻል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት የሚዲያ ሀላፊ ዋና […]

በኢትዮጵያ የሚከበረው የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀን መረጃ ለህዝብ ጥቅም በሚል መሪ ሀሳብ ነው ለ30ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው። ከ 30 አመት በፊት በናሚቢያ መከበር የጀመረው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ መንግስታት የፕሬስ ነፃነትን እንዲያከብሩ መነሻ ሆኗል። በኢትዮጵያ የሚከበረውን አለምአቀፉ የፕሬስ ቀን በማስመልከት አዲስ አበባ ውስጥ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡ በሀገራችን የፕሬ […]

በአዲስ አበባ በደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013  በአዲስ አበባ ከተማ በደረሱ ሁለት ድንገተኛ አደጋዎች የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አያት ጤና ጣቢያ ጀርባ ትናንት ምሽት 2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ በግንባታ ስራ ላይ የነበረ የ35 […]

አጣየን መልሶ ለመገንባት የተጀመረ ጥረት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013  የወጣት ማህበራት የአጣዬ ከተማና አካባቢው ተጎጂዎችን እንዲቋቋሙ ለማገዝ ሃብት ማሰባሰብ ጀመሩ በአማራ ክልል አጣዬ ከተማንና አካባቢው ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም መንግስት የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ ሃብት የማሰባሰብ ሰራ መጀመሩን በክልሉ የወጣት ማህበራት አመራሮች አስታውቀዋል፡፡ የክልሉ ወጣቶች ማህበር ዋና ፀሐፊ ወጣት ከፍያለው ማለፎ ለኢዜአ እንደገለጸው፤ በአጣዬ ከተማ በደረሰው ጉዳት የክልሉን ወጣቶችን አሳዝኗል። […]

ኢትዮጵያ የታገሰችው የሱዳንን ህዝብ ስለምታከብር እንጂ ፈርታ አይደለም!

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 ሱዳን ቤንሻንጉልን የራሷ ለማድረግ የምታደርገው እንቅስቃሴ እጅግ አሳፋሪ መሆኑን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሱዳን የኢጋድ ሊቀመንበር ሆና እያለ በዚህ መንገድ ለመፈፀም የምትሞክረው ህገወጥ ድርጊት በኢትዮጺያ በኩል ፍፅም ተቀባይነት እንደሌለው ነው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የገለፁት፡፡ ሱዳን የኢትዮያን መሬት የመያዟና ኢትዮጵያዊያን አርሶአደረች ማፈናቀሏ ሳያንሳት ቤንሻንጉልን የራስዋ […]

ማህበረሰቡ በሀሰተኛ መረጃ እንዳይታለል የጠቅላይ ሚሴቴር ፅህፈት ቤት አሳሰበ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 ማህበረሰቡ በሀሰተኛ መረጃ እንዳይታለል የጠቅላይ ሚሴቴር ፅህፈት ቤት አሳሰበ፡፡ ጽህፈት ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ የወንጀለኞች ቡድን የሀሰተኛ መረጃ እያሰራጨ መሆኑን ደርሰንበታል ብሏል፡፡ የወንጀለኞች ቡድን አባላቱ ከቀድሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የግል የኢሜይል አድራሻ የተላከ በማስመሰል መረጃ በመጠየቅ እና ሐሰተኛ ምላሽ በመስጠት ላይ መሆናቸውን አውቀናል ነወ ያለው። በመሆኑም ሁሉም ሰው […]