ለሁለት አዲስ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ፈቃዶች ለወጣው ጨረታ 6 ዓለም ዓቀፍ የቴሌኮም ድርጅቶች ሰነድ አስገቡ፡፡
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 ለሁለት አዲስ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ፈቃዶች ለወጣው ጨረታ 6 ዓለም ዓቀፍ የቴሌኮም ድርጅቶች ሰነድ አስገቡ፡፡ የጨረታ ማስገቢያው ጊዜ ዛሬ ጠዋት 4 ሰዓት ላይ ተጠናቋል። በዚህም ለሁለቱ አዲስ የቴሌኮሙኒኬሽን ፈቃዶች ሳፋሪኮም ከኬንያ ፣ቮዳፎን ከብሪታኒያ ፣ቮዳኮም ከደቡብ አፍሪካ፣ ሲዲሲ ግሩፕ ከብሪታኒያ፣ ሰሚቶሞ ኮርፖሬሽን ከጃፓን እና ኤምቲኤን ግሩፕ ከደቡብ አፍረካ ሰነዶቻቸውን ማስገባታቸውን ገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። […]