loading
የቱርክ የፊልም ኢንዱስትሪም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን እያጠናከረ ነው-ጠ/ሚ ዐቢይ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13፣2013 የለውጥ ሂደቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ኢትዮጵያና ቱርክ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር በጋራ እየሰሩ ነው:: ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያና ቱርክ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር የሚያስችሉ ተጨማሪ  ስምምነቶችን ተፈራርመዋል። በቱርክ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል። ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን በመግለጫቸው ሁለቱ አገሮች ያላቸው ግንኙነት ወንድማማችነት ነው ብለዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው […]

ህወሓትን ሲደግፉ የነበሩ ግለሰቦችን ለህግ ለማቅረብ ከኢንተርፖል ጋር እየሰራን ነዉ-ፌደራል ፖሊስ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13፣2013  ለአሸባሪው ህወሓት የኢኮኖሚ ምንጭ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ 117 የንግድ ድርጅቶች እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ህገወጥ ምንዛሪን አስመልክቶ ለአርትስ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ባካሄደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ለሽብር ቡድኑ የኢኮኖሚ ምንጭ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩ የንግድ ድርጅቶች እና መኖሪያቤቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ የአሸባሪው ቡድን የፋይናንስ ምንጭ […]

በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚገኙ ታዳጊዎች የቡሄ በዓልን በማስመልከት ለህዳሴ ግድብ ገንዘብ አሰባሰቡ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13፣2013  በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚገኙ ታዳጊ ኢትዮጵያዊያን የቡሄ በዓልን በማስመልከት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አካሄዱ በፕሮግራሙ ላይም በቡሄ ጭፈራ የታጀቡ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡ ታዳጊዎቹ ካስተላለፏቸዉ መልዕክቶች ውስጥ የግድቡ መጠናቀቅ ህጻናትና ታዳጊዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ በመከታተል የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ ያስችላቸዋል የሚለው ይገኝበታል፡፡ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው መረጃውን ያጋሩት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ የሁሉም […]