loading
በአዲስ አበባ ትላንት በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ከአንድ ቤተሰብ 5 ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል-ተጎጂዎች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣2013  በመዲናዋ ትናንት በተከሰተ የጎርፍ አደጋ እስካሁን የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ:: የአዲስ አበበ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰለሞን ፍሰሃ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በተከሰተው አደጋ በህይወት እና ንብረት ላይ የደረሱ ጉዳቶች እየተጣሩ ነው፡፡ እስካሁን በአደጋው የ7 ሰዎች ህይወት ማለፉን የገለጹት ኮሚሽነሩ÷አጠቃላይ የደረሰው ጉዳት ዛሬ ከሰዓት ይፋ እንደሚደርግም ጠቁመዋል፡፡ በመካነየሱስ […]

በሳዑዲ አረቢያ እስርቤቶች የሚገኙ ኢትጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ሊመለሱ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣2013 በሳዑዲ አረቢያ የተለያዩ ማቆያ ማእከላትና እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ተገለፀ፡፡ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት በሪያድ የሚገኘነውን የኢትዮጵያ ኤምባሲን ጠቅሶ በፌስቡክ ገጹ እንዳሰፈረው፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ጋር በመቀናጀት በሳምንት ሶሶት በረራዎችን በማድርግ በሳዑዲ አረቢያ የተለያዩ ማቆያ ማዕከላትና እስር ቤቶች የሚገኙ ዜጎችን ከዚህ […]

በኒውዚላንድ አንድ የኮቪድ-19 ተጠቂ መገኘቱን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ዕቀባ ተጣለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣2013 በኒውዚላንድ አንድ የኮቪድ-19 ተጠቂ መገኘቱን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ገደብ መጣሉ ተነገረ፡፡በኒው ዚላንድ በስድስት ወር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ፤ ኦክላንድ ውስጥ አንድ ሰው የኮቪድ-19 ተህዋሲ ተጠቂ መሆኑን ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ ከሶስት ቀን እስከ ሳምንት የሚደርስ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ታውቋል። በተህዋሲው የተያዘው ሰው የተጎበኘችው የባህር ዳርቻዋ ከተማ ኮሮማንዴል እንደ ኦክላንድ ሁሉ ለሰባት ቀናት […]

51 ሺህ 89 ኢትዮጵያዊያን ከሀገር ወጥተው የት እንዳሉ አይታወቅም::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣2013 ከሀገር ውጪ ፈልሰው አድራሻቸው ያልታወቁ 51 ሺ 89 ዜጎች መኖራቸውን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ኤጀንሲው የአለማቀፍ ፍልሰት ድርጅት እና ዳኒሽ ከተባለ ግብርሰናይ ድርጅት ጋር በመተበባር ባስጠናው ጥናት 51 ሺ 89 ኢትዮጵያዊያን ከሀገር እንደወጡ የት እንዳሉ እንዳልታወቀ ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡ ከ41 ሺህ በላይ ቤተሰቦች ለተካተቱበት ለዚህ ጥናት የኢትዮጵያ መንግስት 36 ሚሊዮን ብር ያወጣበት […]

በአፍጋኒስታን ጉዳይ አሁንም አቋሜ የጸና ነው -ጆ ባይደን

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣2013  የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከአፍጋኒስታን ወታደሮቼን በማውጣት ውሳኔዬ የምጸጸትበት አይደልም ሲሉ ተናገሩ፡፡ አንድም የአሜሪካ ወታደር በአፍጋኒሰታን ምድር ሊሞት አይገባም ያሉት ባይደን በአወጣጥ ላይ ክፍተቶች እንደነበሩ አልሸሸጉም፡፡ ጆ ባይደን ማስተባበያ በሰጡበት በዚህ ንግግራቸው እንዳብራሩት፣ የአፍጋኒሰታን ጦር ታሊባንን ለመዋጋት ፍላጎት እንዳልነበረው፤ የአፍጋኒሰታን መንግሥትም ወዲያውኑ ተስፋ እንደቆረጠ ከገለጹ በኋላ ፤ታሊባን ካቡልን ይቆጣጠራል ብለን ከገመትንበት […]