loading
አሸባሪዉ ህዉሃት ሰቆጣን ለመቆጣጠር ያደረገዉ ተደጋጋሚ ሙከራ እንዳይሳካ የሰቆጣ ወጣቶች ተደራጅተዉ ያበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነዉ ሲል ተደራጅተዉ አከባቢያቸዉን ከሚጠብቁ ወጣቶች አንዱ የሆነዉ ሙሉቀን ዳኘዉ ለአርትስ በስልክ ያደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 አሸባሪዉ ህዉሃት ሰቆጣን ለመቆጣጠር ያደረገዉ ተደጋጋሚ ሙከራ እንዳይሳካ የሰቆጣ ወጣቶች ተደራጅተዉ ያበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነዉ ሲል ተደራጅተዉ አከባቢያቸዉን ከሚጠብቁ ወጣቶች አንዱ የሆነዉ ሙሉቀን ዳኘዉ ለአርትስ በስልክ ያደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡ በተለይም የተደራጀዉ የአካባቢዉ ወጣት ሃይል ህዝቡ ከተማውን ለማንም ጥሎ እንዳይወጣ የማረጋጋትና ማንኛውም የታጠቀ ሃይል በአንድ ኮማንድ ስር ሆኖ በፈረቃ ከተማውን እንዲጠብቅ በማድረግ […]

በህገወጥ መንገድ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ በማስገጠም  ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የማያውቀውን የኤሌክትሪክ ቆጣሪ በማስገጠም የኤሌክትሪክ ሃይል ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦች እና ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ። የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ሰፈራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑ ተመላክቷል። በአካባቢው የሚኖሩ አምስት ግለሰቦች የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ለማስገባት ፈልገው ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ  አገልግሎት ምስራቅ […]