loading
አዲስ አበባ እና ድሬዳዋን ጨምሮ በአራት ክልሎች የዕጩዎች ምዝገባ ዛሬ ይጀመራል::

አዲስ አበባ፣የካቲት 8፣ 2013 አዲስ አበባ እና ድሬዳዋን ጨምሮ በአራት ክልሎች የዕጩዎች ምዝገባ ዛሬ ይጀመራል:: አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ኦሮሚያ እና ሐረሪ ክልሎች የዕጩዎች ምዝገባ ዛሬ ይጀመራል። ምዝገባው የሚከናወነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዕጩዎች ምዝገባ ባወጣው ከየካቲት 08 እስከ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ነው። የምርጫ […]

ዩናይትድ አርብ ኤሚሬት በእስራኤል የሚያገለግላትን አምባሳደር ሰየመች፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 8፣ 2013 ዩናይትድ አርብ ኤሚሬት በእስራኤል የሚያገለግላትን አምባሳደር ሰየመች፡፡ መሃመድ አል ካጃ በእስራኤል የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አምባሳደር ሆነው ተሾመዋል፡፡ መሃመድ አል ካጃ በሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ፣ ጠ/ሚኒስትር እና የዱባይ ገዥ ሼክ መሀመድ ቢን ራ ሺድ ፊት እሁድ ዕለት በአቡ ዳቢ የአል-ዋታን ቤተመንግስት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ ሚስተር አል ካጃ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን ሕገ- መንግስት እና ሌሎች ህጎች በማክበር ለብሔራዊ ጥቅሟ መከበር ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩ ቃል […]

በዋግኽምራ ዞን 150 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመረቀ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 8፣ 2013 በዋግኽምራ ዞን 150 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመረቀ፡፡ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ድሃና ወረዳ 150 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመርቋል። በምርቃቱ ላይ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰም ማሞና የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮን ጨምሮ የክልልና የብሔረሰብ አስተዳደሩ ከፍተኛ […]

ጊኒ የኢቦላ ቫይረስ በወረርሽኝ ደረጃ መከሰቱን ይፋ አደረገች።

አዲስ አበባ፣የካቲት 8፣ 2013 ጊኒ የኢቦላ ቫይረስ በወረርሽኝ ደረጃ መከሰቱን ይፋ አደረገች። በጊኒ ደቡብ ምስራቅ በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ለህልፈት ከተዳረጉት ሰዎች ባሻገር አራት ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተነግሯል። በደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው ጎዋኬ በአንድ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ የተሳተፉ 7 ሰዎች የማስመለስ፣ የመድማት እና ማስቀመጥ  እንዳጋጠማቸው ተጠቁሟል። የኢቦላ ቫይረስ የተገኘባቸው እነዚህ ሰዎች አሁን ላይ […]