የተፈናቀሉ ዜጎች በምርጫው የሚሳተፉበት አሰራር መዘጋጀቱን ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ገለጹ፡፡
አዲስ አበባ፣ጥር 28፣ 2013 የተፈናቀሉ ዜጎች በምርጫው የሚሳተፉበት አሰራር መዘጋጀቱን ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ገለጹ፡፡ የተፈናቀሉ ዜጎች በ6ኛው አገራዊ ምርጫ የሚሳተፉበት አሰራር መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ገለጸዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ”ይጠይቁ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የማህበራዊ ሚዲያ የተሳትፎ መድረክ ለቀረቡ ጥያቄዎች በቦርዱ የፌስቡክ ገጽ በቀጥታ ምላሽ ሰጥተዋል። […]