loading
የሊቢያ ተፋላሚ ኃይሎች ስምምነት

አዲስ አበባ፣ጥር 17፣ 2013  የሊቢያ ተፋላሚ ኃይሎች ቁልፍ የመንግስት ተቋማትን የሚመሩ እጩዎችን ለመምረጥ ተስማሙ ::የሁለቱም ወገኖች ተወካዮች ሞሮኮ ላይ ባደረጉት አዲስ ውይይት የእጩዎቹ የምልመላ ሂደት ከማክሰኞ ጀምሮ እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡ ተፋላሚ ሃይሎቹ የደረሱበት ስምምነት በሀገሪቱ ለአስር ዓመታት የተካሄደውን የእርስ በርስ ጦርነት እንዲያበቃ ለማድረግ ሁነኛ መፍትሄ መሆኑ ነው የተመገረለት፡፡ ሂደቱ እስከመጭው ፌብሩዋሪ 2 ቀን ድረስ የሚጠናቀቅ ሲሆን […]

በሩሲያ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ::

አዲስ አበባ፣ጥር 17፣ 2013 በሩሲያ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ:: የሩሲያ የፀጥታ ሃይሎች ከ3 ሺህ በላይ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ማሰራቸው ተሰማ ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት በቅርቡ ከህመም ያገገሙት የተቃዋሚ መሪው አሌክስ ናቫልኒ ከእስር ይፈቱልን የሚል ጥያቄ ይዘው ነው፡፡

በእንግሊዝ በሙከራ ሂደት ላይ ያለው የኮቪድ-19 ክትባት መልካም ውጤት እያሳየ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 21፣ 2013 በእንግሊዝ በሙከራ ሂደት ላይ ያለው የኮቪድ-19 ክትባት መልካም ውጤት እያሳየ ነው ተባለ፡፡ የክትባቱ የውጤታማነት ደረጃ ሲለካ 89 ነጥብ 3 በመቶ እንደሆነ የእንግሊዝ የጤና ባለሙያዎች ይፋ ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ይህን መልካም ዜና እንደሰሙ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡ ኖቫቫክስ የተባለው ይህ ክትባት አዲሱን የኮሮናቫይረስ ዝርያ በመከላከል ውጤታማ ሆኖ የተገኘ […]

የማዕከላዊ አፍሪካ ዜጎች ወደጎረቤት ዲሞክራቲክ ኮንጎ መጠለያ ፍለጋ እየተሰደዱ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 21፣ 2013 የማዕከላዊ አፍሪካ ዜጎች ወደጎረቤት ዲሞክራቲክ ኮንጎ መጠለያ ፍለጋ እየተሰደዱ ነው ተባለ፡፡ ስደተኞቹ ቀያቸውን ጥለው የሚሰደዱት በሀገሪቱ ነፍጥ አንግበው ከሚዋጉ ሚሊሻዎች ጥቃት ህይዎታቸውን ለማዳን ሲሉ ነው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በአሁኑ ወቅት ከማዕከላዊ አፍሪካ ወደ ጎረቤትረ ዲሞክራቲክ ኮንጎ የተሰደዱ 30 ሺህ ዜጎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖራሉ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት […]