loading
የተማሪዎችን የፈጠራ ውጤቶች በአግባቡ መምራት የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣ 2013 የተማሪዎችን የፈጠራ ውጤቶች በአግባቡ መምራት የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ:: የትምህርት ሚኒስቴር በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና፣ በጥበብና ሂሳብ ዘርፍ የሚቀርቡ የተማሪዎችን የፈጠራ ስራዎች ከዚህ በፊት ከነበረው አሰራር ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ረቂቅ መመሪያ ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ መመሪያው ተወዳዳሪዎች በተቀመጠላቸው መስፈርት መሰረት የፈጠራ ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡና አሸናፊዎች በማያሻማ መልኩ ተለይተው ተገቢውን ማበረታቻ እንዲያገኙ የሚያግዝ መሆኑ ነው […]

በጋምቤላ ክልል በሰለጠነ ባለሙያ የወለዱ እናቶች ሽፋን 40 በመቶ መሆኑ ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣ 2013 በጋምቤላ ክልል በሰለጠነ ባለሙያ የወለዱ እናቶች ሽፋን 40 በመቶ መሆኑ ተገለፀ:: በክልሉ የእናቶችና ጨቅላ ህፃናትን ጤናና የስርዓተ ምግብ ሁኔታን ለማሻሻል ያለመ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል፡፡ በዚህ ወቅት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳሉት በክልሉ በሰለጠነ ባለሙያ የሚወልዱ እናቶች ሽፋን 40 በመቶ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ሚኒስትሯ የህጻናት ክትባት መሻሻል ቢታይበትም አሁንም ዝቅተኛ ሽፋን እንዳለው […]

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በተከሰተ የፀጥታ መደፍረስ 123 ሰዎች ሲገደሉ 500 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣ 2013 የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በተከሰተ የፀጥታ መደፍረስ 123 ሰዎች ሲገደሉ 500 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተባለ:: የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የምርመራውን ግኝቶች ይፋ ባደረገበት ወቅት በወንጀሉ የተሳተፉ ሰዎች ያደረሱት ጥቃት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ባሕርያትን የሚያሟሉ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡

እስራኤል በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2020 በጋዛ ሰርጥ 300 ጥቃቶችን መፈፀሟን ይፋአደረገች::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣ 2013 እስራኤል በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2020 በጋዛ ሰርጥ 300 ጥቃቶችን መፈፀሟን ይፋአደረገች:: የሀገሪቱ መከላከለያ ተቋም ባወጣው መግለጫ በአካባቢው በተመረጡ 300 ኢላማዎችላይ ጥቃት ማድረሱንና 38 የጥቃት ሙከራዎችን ማክሸፉን ተናግሯል፡: ከጋዛ በኩል 176 ሮኬቶች ተተኩሰውብን ነበር ያለው የእስራኤል ጦር ሃይል ከነዚህ ውስጥ 90 በመቶ የሚሆኑት ባዶ ሜዳ ላይ ነው ያረፉት ብሏል፡፡ በሪፖርቱ እንደተገለፀው የእስራኤል ተዋጊ […]

አፍሪካ ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር እየታገለች ነው ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣ 2013 አፍሪካ ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር እየታገለች ነው ::ከቀሪው ዓለም ጋር ሲነፃፀር የበሽታው ስርጭት በአፍሪካ አነስተኛ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥሩ እየጨመረ መምጣቱ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት አሁን ላይ በ47 የአፍሪካ ሀገራት በበሽታው የተያዙባቸው ዜጎች ሳምንታዊ አማካይ ቁጥር 73 ሺህ መድረሱ ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በአፍሪካ አህጉር የበሽታውን የስርጭት መጠን […]