loading
እጅ ንክኪ ነፃና ለአጠቃቀም ቀላል የእጅ ማስታጠቢያ የፈጠራ ውድድር ምዝገባ ተጀመረ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ08፣ 2012 ከእጅ ንክኪ ነፃና ለአጠቃቀም ቀላል የእጅ ማስታጠቢያ የፈጠራ ውድድር ምዝገባ ተጀመረ::ውድድር በዩ. ኤስ. ኤድ ትራንስፎርም ዋሽ እና ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ትብብር ነዉ የተዘጋጀዉ፡፡ የውድድሩ አዘጋጆች በሰጡት መግለጫ ማንኛውም በቴክኒክና ሞያ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችም ይሁኑ በቴክኖሎጂ ፈጠራ ላይ የሚሰሩ ግለሰቦች መወዳደር ይችላሉ፡፡በሚኒስቴሩ የጤና አጠባበቅ ምክትል ዳይሬክተር አቶ አሽረፈዲን ዮያ እንደተናገሩት ህብረተሰቡ በንክኪ የሚተላለፉ […]

ሶማሊያ ሞቃዲሾ ከተማ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 17 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸው ተሰምቷል::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 11፣ 2012 ሶማሊያ ሞቃዲሾ ከተማ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 17 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸው ተሰምቷል:: የሀገሪቱ መንግስት ቃል አቀባይ ኢስማኤል ሙክታር ኦማር እንዳሉት ጉዳቱ የደረሰው የአልሸባብ ታጣቂዎች በአንድ ሆቴል በከፈቱት ጥቃት ነው፡፡ ቃል አቀባዩ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ጥቃቱን ያደረሱት አራቱም የአልሸባብ ታጣቂዎች በተኩስ ልውውጡ ወቅት በመንግስት የፀጥታ ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ከሶስት ሰዓታት በላይ በፈጀው የተኩስ […]

ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅ አቋርጠውት የነበረውን ድርድር ለመጀመር ተስማሙ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 11፣ 2012ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅ አቋርጠውት የነበረውን ድርድር ለመጀመር ተስማሙ:: የሱዳን የውሃ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ረዘም ካለ ውይይት በኋላ ሶስቱም ሀገራት በየራሳቸው ያዘጋጇቸውን የውይይት ሀሳቦች በማስታረቅ ከማክሰኞ ጀምሮ ለመደራደር ተስማምተዋል ብሏል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው በሳምንቱ መጨረሻ ካርቱም ላይ ተገናኝተው የተዋያዩት የግብፅ እና የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ቀጣዩ የሶስቱ ሀገራት ድርድር ፍሬያማ እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ ሁለቱ […]

የቀድሞዋ የአሜሪካ ቀደማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማ ትራምፕ አሜሪካን ከችግር የመታደግ አቅም የላቸውም አሉ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 የቀድሞዋ የአሜሪካ ቀደማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማ ትራምፕ አሜሪካን ከችግር የመታደግ አቅም የላቸውም አሉ:: ቀዳማዊት እመቤቷ ፕሬዚዳንቱ ውጤት ያለው ስራ ሰርቶ ለማሳየት ከበቂ በላይ ጊዜ ተሰጥቷቸዋል ግን አንድም ፍርያማ ተግባር አላከናወኑም ብለዋል፡፡ ትራምፕ ለሀገራችን ትክክለኛው መሪ አይደሉም ያሉት ሚሼል አንድ ቀላል ምሳሌ ብናነሳ የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ በአሜሪካ የተከሰተውን ሁኔታ ማረጋጋት አልቻሉም […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስር ሹመቶችን ዛሬ ሰጡ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስር ሹመቶችን ዛሬ ሰጡ:- – ዶ/ር ቀንዓ ያደታ የመከላከያ ሚኒስትር – ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ፤ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ – ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር – ታከለ ኡማ፤ የማዐድንና ነዳጅ ሚኒስትር – ተስፋዬ ዳባ፤ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ – ዮሐንስ ቧያለው፤ የኢትዮጵያ የውጭ ግነኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት […]

በሊባኖስ የሚኖሩ 450 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ ፈቃድ አገኙ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 በሊባኖስ የሚኖሩ 450 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ ፈቃድ አገኙ:: በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ቆንላ ጀነራል ተመስገን ዑመር ጽሕፈት ቤቱ በሊባኖስ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ዜጎች መረጃዎች ለአገሪቱ ኢምግሬሽን ጉዳዮች መሥሪያ ቤት አስገብቶ እንደነበር ለኢዜአ ገልጸዋል። በዚሁ መሠረት የኢሚግሬሽን ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስፈላጊውን ማጣራት ካደረገ በኋላ 450 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ፈቃድ […]

ኢንጂኔር ታከለ ኡማ በከንቲባነት ዘመናቸው ላደረጉላቸው ድጋፍ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን አመሰገኑ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 ኢንጂኔር ታከለ ኡማ በከንቲባነት ዘመናቸው ላደረጉላቸው ድጋፍ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን አመሰገኑ:: ከአዲስ አበባ ከንቲባነት ቦታቸው ተቀይረው የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ሆነው የተሸሙትምክትል ከንቲባው በነበራቸው የሁለት ዓመት የሥራ ዘመን የከተማዋ ነዋሪዎች እና የስራ ባለደረቦቻቸው ድጋፍ እንዳልተለያቸው በፅህፈት ቤታቸው ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ላይ አስፍረዋል፡፡ በታሪክ አጋጣሚ ይህችን ታሪካዊ ከተማ ለመምራት የተገኘውን ትልቅ ዕድል ላለማባከን […]

ሱዳናዊያን በሀገሪቱ የስልጣን መጋራት ስምምት የተደረገበትን አንደኛ ዓመት በማስመልከት ሰልፍ አካሂደዋል::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 ሱዳናዊያን በሀገሪቱ የስልጣን መጋራት ስምምት የተደረገበትን አንደኛ ዓመት በማስመልከት ሰልፍ አካሂደዋል:: ነዋሪዎቹ ካርቱም ውስጥ ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ አሁን ባለው የሉዓላዊ ምክር ቤት አስተዳደር ቅሬታ እንደገባቸው ተናግረዋል፡፡ ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት ፕሬዚዳንት አልበሽርን በሃይል ከስልጣናቸው ያስወገዱት ጄኔራሎችና ህዝቡን ወክለው ስልጣን የተጋሩት ፖለቲከኞች ሀገር መምራት ከጀመሩ አንድ ዓመት ቢያስቆጥሩም የተፈለገው ለውጥ አልመጣም በማለት ነው፡፡ […]

የሞሳድ ሹም በአቡዳቢ

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13፣ 2012 የሞሳድ ሹም በአቡዳቢ የእስራኤሉ ሞሳድ የስለላ ድርጅት ሀላፊ በደህንነት ዙሪያ ለመወያየት አቡዳቢ ገብተዋል:: ሀላፊው ዮሲ ኮኸን እስራኤል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የዲፕሎማሲ ስምምነት ከተፈራረሙ ወዲህ አቡዳቢን የጎበኙ የመጀመሪያው ባለ ስልጣን ሆነዋል፡፡ ኮኸን ከኤሜሬቶች የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሼክ ታኑም ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ሁለቱ ሀገራትበደህንነት እና ፀጥታ ዙሪያ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች […]

አንድ የቻይና ከፍተኛ ዲፒሎማት በሁለቱ ኮሪያዎች ጉዳይ ለመምከር ወደ ደቡብ ኮሪያ ሊጓዙ ነው::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13፣ 2012 አንድ የቻይና ከፍተኛ ዲፒሎማት በሁለቱ ኮሪያዎች ጉዳይ ለመምከር ወደ ደቡብ ኮሪያ ሊጓዙ ነው:: በሰሜን እና ደቡብ ኮሪያዎች መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተባባሰ የመጣው ውጥረት ተሟሙቆ የነበረውን አዲስ ግንኙነት ጥላ አጥልቶበታል፡፡ ሁለቱ ሀገራት በድንበር አካባቢ ቀለል ያለ የተኩስ ልውውጥ እስከማድረግ ያደረሳቸው ግጭት ውስጥ መግባታቸው ሳያንስ ለሽምግልና በሮቻቸውን መዝጋታቸውም ስጋቱን ከፍ አድርጎታል፡፡ ከሴኡል […]