loading
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢ- ኮሜርስ ግብይት 2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ሽያጭ ማከናወኑን አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ሐምሌ16፣ 2012  የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢ- ኮሜርስ ግብይት 2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ሽያጭ ማከናወኑን አስታወቀ፡፡ ኮሮናቫይረስ መከሰቱም ለአየር መንገዱ ኪሳራ ቢያስክትልም በቴክኖሎጂ ዘርፍ ግን አዲስ ምዕራፍ እንዲከፍት እንዳስቻለዉ ገልጿል፡፡ የአየርመንገዱ የኢንትግሬትድና ኮሚኒዩኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር አቶ ምረትአብ ተክላይ ለአርትስ እንደተናገሩት ፤በአቪየሽን ኢንዱስትሪ በዉደድሩ ለማለፍ እና ለማሸነፍ ቴክኖሎጂ ትልቁ ምሶሶ በመሆኑ አየር መንገዱ በዘርፉ ጠንክሮ […]

የግድቡ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት ኢትዮጵያን ወደ ከፍተኛ እድገት የሚያመጣ ወሳኝ ምዕራፍ ነው ሲሉ ምሁራን ተናገሩ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ16፣ 2012የግድቡ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት ኢትዮጵያን ወደ ከፍተኛ እድገት የሚያመጣ ወሳኝ ምዕራፍ ነው ሲሉ ምሁራን ተናገሩ::የህዳሴው ግድቡ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት ኢትዮጵያን ወደ ከፍተኛ የስልጣኔና ምጣኔ ሀብታዊ እድገት የሚያመጣ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተናገሩ።ምሁራኑ ለኢዜአ እንዳሉት የግድቡ ቀሪ ግንባታ ተጠናቆ የተሟላ አገልገሎት እንዲጀምር እያንዳንዱ ዜጋ ተቀናጅቶና ተባብሮ መደገፍ ይጠበቅበታል።በዩኒቨርሲቲው […]

የመከላከያ ሠራዊት አባላት በሕዳሴው ግድብ ለፈጸሙት አኩሪ አገራዊ ተልዕኮ ምስጋና ተቸራቸው:

አዲስ አበባ፣ሐምሌ16፣ 2012የመከላከያ ሠራዊት አባላት በሕዳሴው ግድብ ለፈጸሙት አኩሪ አገራዊ ተልዕኮ ምስጋና ተቸራቸው::የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ መሰረት ጀምሮ አስካሁን ድረስ ለፈጸሙት አኩሪ አገራዊ ተልዕኮ በመከላከያ ሚኒስቴር ምስጋና ተቸራቸው። ሚኒስቴሩ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግደብ የመጀመሪያ ምዕራፍ ውሃ ሙሌት መጠናቀቁን ተከትሎ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሃመድ ተሰማ ለኢዜአ በላኩት […]

በጎንደር ከተማ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች የተገኘበት ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ16፣ 2012 በጎንደር ከተማ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች የተገኘበት ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ::በጎንደር ከተማ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች በመኖሪያ ቤቱ ተገኝቶበታል የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማው የሰላምና የህዝብ ደህንነት መምሪያ አስታወቀ፡፡የመምሪያው ምክትል ኃላፊ አቶ አንደበት ከበደ ለኢዜአ እንደተናገሩት ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው በጎንደር ማራኪ ክፍለ ከተማ መኖሪያ ቤቱ ውስጥ የተደበቀ የጦር መሳሪያዎች ተገኝቶበት ነው።ከግለሰቡ […]

ሰሞኑን ፈረንሳይ ውስጥ በተቀሰቀሰ የእሳት አደጋ ሁለት ህፀናትን ያዳኑ ሰዎች ከከንቲባቸው ጀግኖች የሚል ውዳሴ ተችሯቸዋል::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ16፣ 2012ሰሞኑን ፈረንሳይ ውስጥ በተቀሰቀሰ የእሳት አደጋ ሁለት ህፀናትን ያዳኑ ሰዎች ከከንቲባቸው ጀግኖች የሚል ውዳሴ ተችሯቸዋል::የሶስት እና የአስር ዓመት ያላቸው እመነዚህ ህፃና የሚኖሩበት አፓርታማ በእሳት ሲጋይ ከሶስተኛ ፎቅ መውጫ አጥተው ህዝቡ ከታች ከቦ ይመለከት ነበር፡፡ሰዎቹም ህፀናቱ በመስኮት እንዲዘሉ እና ጉዳት ሳይደርስደባቸው እንደሚቀበሏቸው በማበረታታት የህፀናቱን ህይዎት መታግ ችለዋል ነው የተባለው፡፡ህፀናቱም እሳቱ እየበረታ ሲመጣ ከንጻው ስር […]

በአፍሪካ ከ10 ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ19 መያዛቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ አደረገ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ17፣ 2012 በአፍሪካ ከ10 ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ19 መያዛቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ አደረገ:: ድርጅት ባወጣው ሪፖርት የሄን ያህል ቁጥር ያላቸው የጤና ባለሙያዎች በበሽታው የተያዙት በ40 የአፍሪካ ሀገራት ነው፡፡ ድርጅቱ የጤና ባለሞያዎቹ በአህጉሩ በፍጥነት እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ወደ ኋላ የሚጎትት ፈተና ነው ብሏል፡፡ ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት […]

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህገ ወጥነትን ለመከላከል በርካታ የፌደራል ሀይሎችን አሰማራለሁ አሉ ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ17፣ 2012 ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህገ ወጥነትን ለመከላከል በርካታ የፌደራል ሀይሎችን አሰማራለሁ አሉ ::ፕሬዚዳንቱ ከፎክስ ኒውስ ጋር በስልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እስከ 75 ሺህ ወታደሮችን በሁሉም የአሜሪካ ከተሞች ለማሰማራት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ይሁን እንጂ ይህን የምናደርገው ከየግዛቶቹ የድጋፍ ጥያቄ ከቀረበልን ነው ያሉት ትራምፕ አግዙን የሚሉን ከሆነ ያለማቅማማት እናደርገዋለን ብለዋል፡፡ የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ […]

ኢትዮጵያ እና ጃፓን የ490 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ17፣ 2012 ኢትዮጵያ እና ጃፓን የ490 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ::ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ማትሱናጋ ዳይሱኬ ተፈራርመውታል፡፡ ገንዘቡ በኢትዮጵያ ኪቪድ19ኝን ጨምሮ በጤናው ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግና ለህክምና ቁሳቁስ መግዣ የሚውል ነው ተብሏል፡፡ ሁለቱን የከተማ አስተዳደሮች ጨምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ሆስፒታሎች ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን በማቅረብ የጤና ስርአቱን ለማዘመን ለሚደረገው […]

እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ሐምሌ17፣ 2012 እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ኮሮና ቫይረስን ምክንያት በማድረግ ሊፈጠር የሚችል ተገቢነት የሌለው የዋጋ ግሽበትን ለመከላከልና የምርት እጥረት እንዳይከሰት በተሰራ የተቀናጀ ስራ ከክልል አምራች ኅብረት ሥራ ማኅበራት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል፡፡ ከተሰበሰበው ምርት ውስጥ ከ875 ሺህ […]

ሱዳን ወሳኙ የህዳሴው ግድብ ድርድር እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበች::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ20፣ 2012 ሱዳን ወሳኙ የህዳሴው ግድብ ድርድር እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበች::የሱዳን የመስኖና የውኃ ሀብት ሚኒስቴር ቀጣዩ ወሳኝ ድርድር ቁርጥ ያለ ጊዜ ተይዞለት ግልፅ በሆኑ አጀንዳዎች ላይ አተኩሮ እደካሄድ የሚል ጥሪ አቅርቧል፡፡ሚኒስቴሩ በመግለጫው ድርድሩ የሁሉንም ወገኖች ጥቅም የሚያስጠብቀና ከሚታወቁት አጀንዳዎች ውጭ የሆኑ ሀሳቦች ሳይካተትበት ወደ ውይይቱ መግባተ ያስፈጋል ሲልም አሳስቧል፡፡ሲ ጂ ቲ ኤን እንደዘገበው ካርቱም ባለፈው […]