loading
በኮቪድ 19 ምክንያት የትጎዱ የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪዎችን ለመደገፍ እና ለማነቃቃት ያለመ የ30 ኪ.ሜ የብስክሌት ውድድር ማዘጋጀቱን ቱሪዝም ኢትዮጵያ አስታወቀ።

አዲስ አበባ፣ ህዳር 07፣ 2013 በኮቪድ 19 ምክንያት የትጎዱ የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪዎችን ለመደገፍ እና ለማነቃቃት ያለመ የ30 ኪ.ሜ የብስክሌት ውድድር ማዘጋጀቱን ቱሪዝም ኢትዮጵያ አስታወቀ።ከዚህ ቀደም በቱሪዝም ዘርፍ ተሰማርተው የነበሩ ባለሀብቶች እና አገልግሎት ሰጪዎች በኮቪድ ምክንያት ተስፋ ቆርጠው ከዘርፉ በመውጣት ላይ ይገኛሉ በዚህም ምክንያት የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት እና ወደ ስራ ለማስገባት ያለመ የተራራ ላይ ቱሪዝም ማዘጋጀቱን […]

መንግስት ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚሰደዱ ዜጎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ አስታወቁ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 08፣ 2013 መንግስት ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚሰደዱ ዜጎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ አስታወቁ:: የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚሰደዱ ወገኖችን ለመቀበል እና ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስት ዐቢይ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የተሰደዱ ንፁሀን ዜጎችን ንብረታቸውን ለመጠበቅ ፣ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰብአዊ ድጋፍ ለማቅረብ እና […]

በኢትዮጵያ አየር ሀይል እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተ የሀሰት መረጃዎች እየወጡ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 08፣ 2013 በኢትዮጵያ አየር ሀይል እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተ የሀሰት መረጃዎች እየወጡ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ፡፡ እንደ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በሁለት ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን አማካኝነት፣ በመቀሌ የአየር ጥቃት መደረጉን የሚገልጹ አርዕስት እና አጭር ቪዲዮዎች ወጥቷል፤ እነዚህ መረጃዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ኃይሉ ሳያረጋግጡ በትህነግ መረጃ ላይ […]

የናይጄሪያ ሳይንቲስቶች በዋጋው ርካሽና በፍጥንት ዉጤትን ለማወቅ የሚያስችል የኮቪድ 19 የምርመራ ኪት መስራታቸዉን አስታወቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 08፣ 2013 የናይጄሪያ ሳይንቲስቶች በዋጋው ርካሽና በፍጥንት ዉጤትን ለማወቅ የሚያስችል የኮቪድ 19 የምርመራ ኪት መስራታቸዉን አስታወቁ፡፡ ሲኤን ኤን እንደዘገበዉ ሳይኒቲስቶቹ ሰራነው ያሉት አዲሱ የመመርመሪያ ኪት እርካሽና በቀላሉ ማገኘት ሚያስችል ነዉ ፤ዉጤቱንም ከ 40- ደቂቃ ባነሰ ግዜ ዉስጥ ያሳዉቃል፡፡ የመመርመሪያ ኪቱን ዉጤት የሚያሳዉቅ ማሽን አዲስ የተሰራ ሳይሆን ከዚህ በፊት ለኮቪድ 19 መመርመሪያ የሚዉለዉን […]

በአፍሪካ የኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ቁጥር ከ2 ሚሊዮን ማለፉ ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 09፣ 2013 በአፍሪካ የኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ቁጥር ከ2 ሚሊዮን ማለፉ ተሰማ:: ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ እንዳስታወቀው በአሁኑ ጊዜ በአህጉሩ በወረርሽኙ የተያዙ ሰወች ከ1 ሚሊዮን 986 ሺህ በላይ ደርሰዋል፡፡ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 47 ሺህ 647 መድረሱን የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከለያና መቆጣጠሪያ ማእከል በሪፖርቱ ይፋ አድርጓል፡፡ ሲ ጂ ቲ ኤን እንደዘገበው በበሽታው ከተያዙት […]

ተናሰባቹ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አንድ የምርጫ ደህንነት ባለስልጣንን አባረሩ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 09፣ 2013 ተናሰባቹ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አንድ የምርጫ ደህንነት ባለስልጣንን አባረሩ:: ምርጫው ተጭበርብሯል በሚለው አቋማቸው የጸኑት ትራምፕ የሳይበር እና መሰረተ ልማት ደህንነት ሃላፊ የነበሩትን ክሪስ ክሬብን ነው ያባረሯቸው፡፡ ለክሬብ መባረር ምክንያት የተባለው ደግሞ የዘንድሮው ምርጫ በአሜሪካ ታሪክ ካለፉት ምርጫዎች ሁሉ አስተማማኝና ተዓማኒ ነው የሚል ከትራምፕ በተቃራኒ የቆመ አስተያየት በመስጠታቸው ነው፡፡ ትራምፕ በሰጡት […]

የፖፕ ሙዚ አቀንቃኙና ፖለቲከኛው ሮበርት ኪያጉላኒ መታሰሩን ተከትሎ በዩጋንዳ አመፅ ተቀስቅሷል::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 11፣ 2013 የፖፕ ሙዚ አቀንቃኙና ፖለቲከኛው ሮበርት ኪያጉላኒ መታሰሩን ተከትሎ በዩጋንዳ አመፅ ተቀስቅሷል:: በቅፅል ስሙ ቦቢ ዋን በመባል የሚታወቀው ዩጋንዳዊው ፖለቲከኛን መታሰር ለመቃወም አደባባይ በወጡ ደጋፊዎችና የፀትታ ሰዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት 7 ሰዎች መሞታቸውም ተሰምቷል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ለተቃውሞ አደባባይ ከወጡት ሰዎች መካከል ከ40 በላይ የሚሆኑት የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ ቦቢ ዋይን በዩጋንዳ […]

ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ተቋም በስደት ላይ ያሉ ሰዎች የኮሮቫይረስ ክትባት እንዲያገኙ ጥሪ አቀረበ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 11፣ 2013 ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ተቋም በስደት ላይ ያሉ ሰዎች የኮሮቫይረስ ክትባት እንዲያገኙ ጥሪ አቀረበ:: ተቋሙ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ባቀረበው ጥያቄ ህብረቱ ፍልሰተኞቹ እንደሌላው ዜጋ ሁሉ እኩል ተደራሽነት ያለው የክትባት አገልግሎት ሊያገኙ ይገባል ብሏል፡፡ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አንቶኒዮ ቪቶሪኖ የአንዱ ጤና መሆን ለሌላው ዋስትና ስለሆነ የስደተኞቹን ደህንነት መጠበቅ ጥቅሙ ለነሱ ብቻ ሳይሆን […]

ቻይና እና ጀርመን በኮቪድ-19 ክትባት ስርጭት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያችል ውይይት አደረጉ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2013 ቻይና እና ጀርመን በኮቪድ-19 ክትባት ስርጭት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያችል ውይይት አደረጉ:: የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ከቡድን 20 ጉባኤ በኋላ ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት አውሮፓ በሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስለመጠቃቷና ችግሩን እንዴት በጋራ መፍታት እንደሚቻል ተነጋግረዋል፡፡ የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂምፒንግ ከጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ቻይና ከጀርመን ጋር […]

በደቡባዊ ምስራቅ የህንድ ግዛቶች የተከሰተው አውሎ ንፋስ በርካታ ነዋሪዎችን ስጋት ላይ ጥሏል::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2013 በደቡባዊ ምስራቅ የህንድ ግዛቶች የተከሰተው አውሎ ንፋስ በርካታ ነዋሪዎችን ስጋት ላይ ጥሏል:: ሳይክሎን ኒቫር በመባል የሚታወቀው አውሎ ንፋስ በደቡብ ምስራቅ ህንድ በሚገኙ ሶስት ግዛቶች በፍጥነት እየገሰገሰ መሆኑን ተከትሎ ሰዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ ትእዛዝ ተላልፎላቸዋል፡፡ ሰዎች በአደባባይ እንዳይሰባሰቡና ተጨማሪ መመሪያዎች እስኪተላለፉላቸው ድረስ በጥንቃቄ እንዲቆዩ የአካባቢው ባለስልጣናት አስጠንቅቀዋል ነው የተባለው፡፡ አደጋው ሊያደርስ የሚችልውን […]