ፔፕሲኮ ኢትዮጵያ “ ምግብ ይለግሱ -ተስፋን ይቀጥሉ “የሚል ፕሮግራም ይፋ አደረገ ፡፡
አዲስ አበባ ፣ግንቦት 27፣ 2012 ፔፕሲኮ ኢትዮጵያ “ ምግብ ይለግሱ -ተስፋን ይቀጥሉ “የሚል ፕሮግራም ይፋ አደረገ ፡፡በፕሮግራሙም 2 ሺህ ሰዎችን ለሶስት ወራት ምሳና እራት እንዲመገቡ ይደረጋል፡፡ድርጅቱ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንደስታወቀዉ ፤ ድጋፉ በኢትዮጵያ በኮቪድ 19 ስርጭት ምክንያት ለተጎዱና ጫና ለደረሰባቸዉ አካላት የሚዉል ሲሆን 8ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡ድርጅቱ ድጋፉን ከሜቅዶንያ በጎ አድራጎት ተቋም ጋር […]