loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ሂዝቦላ በእሳት እየተጫወተ ነው ሲሉ አስጠነቀቁ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 22፣ 2012 እስራኤል ሰሞኑን በድንበር አካባቢ ከሂዝቦላ ታጣቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ማድረጓንና የተቃጣባትን ጥቃት በብቃት መመለሷን ተናግራለች፡፡ኔታኒያሁ በሰጡት መግለጫ የሂዝቦላ ታጣቂ ቡድን ሉዓላዊ ድንበራችንን ጥሶ ለመግባት ሙከራ ማድረጉ በእሳት ጨዋታ መሆኑን ሊያውቅ ይባዋል ብለዋል፡፡ለሚቃጣብን ማንኛውም ጥቃት የምንሰጠው የአፀፋ ምላሽ የከፋ መሆኑን አውቆ ቡድኑ አደብ መግዛት አለበት ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠንቅቀዋል፡፡አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው […]

ሩሲያ የመጀመሪያውን የኮቪድ19 ክትባት ለዓለም አበረክታለሁ እያለች ነው

አዲስ አበባ፣ሐምሌ22፣ 2012 የሞስኮ ባለ ስልጣናት እንደሚሉት ከሆነ የኮሮናቫይረስን ክትባት ለመላው ዓለም ለማተዋወቅ ከሁለት ሳምንት ያነሰ ጊዜ ብቻ ነው የቀራቸው፡፡ጋማሊያ ኢንስቲትዩት አገኘሁት ያለውን ክትባት ቢበዛ እስከ ኦገስት 10 ባለው ጊዜ ወስጥ ይፋ አደርጋለሁ ብላለች ሩሲያ፡፡ይሁን እንጂ ሩሲያ ስለ ክትባቱ ሳይንሳዊ ማብራሪያ ከመስጠት መቆጠቧ የውጤታማነቱን ነገር ጥያቄ ውስጥ ይጥለዋል የሚሉ ወገኖች ስጋታቸውን ቀድመው እየገለፁ ነው፡፡ሲ ኤን […]

ሙስሊሙ ማህበረሰብ በዓሉን ሲያከብር ኮቪድ19 በመከላከል ሊሆን እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ22፣ 2012 ሙስሊሙ ማህበረሰብ የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓልን ሲያከብር በእምነቱ የተቀመጡ የወረርሽኝ መከላከያ መንገዶችን እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተቀመጡ ክልከላዎችን ተግባራዊ በማድረግ መሆን እንዳለበት የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር እንድሪስ በዓሉን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡በመግለጫቸውም ሙስሊሙ ማህበረሰብም ይሁን ሌሎች የሀገሪቱ ዜጎች ኮሮናን በመከላከል ጠንካራ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።የዘንድሮውን የአረፋ በዓል የምናከብረው […]

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩንቨርስቲዎች የጣና ሃይቅን ለመታደግ በህብረት እየሰሩ መሆናቸውን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ22፣ 2012 በአማራ ክልል የሚገኙ 10ሩም ዩንቨርስቲዎች የጣናን ሃይቅ ለመታደግ በርካታ የምርምር እና የጥናት ስራዎችን መስራታቸውን ለአርትስ ቲቪ ገልፀዋል፡፡ዩንቨርስቲዎቹ በማህበረሰብ አገልግሎት ፤ በሰላም ግንባታና በእሴት ግንባታ ላይ ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን እየሰሩ መሆናቸውም ነው የገለፁት ፡፡በተለይም በክልሉ የሚገኘውን የጣና ሃይቅ ለመታደግ በርካታ አማራጮች እና ሙከራዎች መደረጋቸውን የወሎ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት እና የአማራ ዩንቨርስቲዎች ሰብሳቢ ዶክተር […]