loading
በአፍሪካ ከ10 ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ19 መያዛቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ አደረገ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ17፣ 2012 በአፍሪካ ከ10 ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ19 መያዛቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ አደረገ:: ድርጅት ባወጣው ሪፖርት የሄን ያህል ቁጥር ያላቸው የጤና ባለሙያዎች በበሽታው የተያዙት በ40 የአፍሪካ ሀገራት ነው፡፡ ድርጅቱ የጤና ባለሞያዎቹ በአህጉሩ በፍጥነት እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ወደ ኋላ የሚጎትት ፈተና ነው ብሏል፡፡ ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት […]

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህገ ወጥነትን ለመከላከል በርካታ የፌደራል ሀይሎችን አሰማራለሁ አሉ ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ17፣ 2012 ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህገ ወጥነትን ለመከላከል በርካታ የፌደራል ሀይሎችን አሰማራለሁ አሉ ::ፕሬዚዳንቱ ከፎክስ ኒውስ ጋር በስልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እስከ 75 ሺህ ወታደሮችን በሁሉም የአሜሪካ ከተሞች ለማሰማራት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ይሁን እንጂ ይህን የምናደርገው ከየግዛቶቹ የድጋፍ ጥያቄ ከቀረበልን ነው ያሉት ትራምፕ አግዙን የሚሉን ከሆነ ያለማቅማማት እናደርገዋለን ብለዋል፡፡ የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ […]

ኢትዮጵያ እና ጃፓን የ490 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ17፣ 2012 ኢትዮጵያ እና ጃፓን የ490 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ::ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ማትሱናጋ ዳይሱኬ ተፈራርመውታል፡፡ ገንዘቡ በኢትዮጵያ ኪቪድ19ኝን ጨምሮ በጤናው ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግና ለህክምና ቁሳቁስ መግዣ የሚውል ነው ተብሏል፡፡ ሁለቱን የከተማ አስተዳደሮች ጨምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ሆስፒታሎች ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን በማቅረብ የጤና ስርአቱን ለማዘመን ለሚደረገው […]

እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ሐምሌ17፣ 2012 እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ኮሮና ቫይረስን ምክንያት በማድረግ ሊፈጠር የሚችል ተገቢነት የሌለው የዋጋ ግሽበትን ለመከላከልና የምርት እጥረት እንዳይከሰት በተሰራ የተቀናጀ ስራ ከክልል አምራች ኅብረት ሥራ ማኅበራት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል፡፡ ከተሰበሰበው ምርት ውስጥ ከ875 ሺህ […]