loading
የአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ የሥራ አጦች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ እንዳሳሰበው ገለፀ

ባለፈዉ ሳምንት ብቻአንድ ነጥብ አምስት አሜሪካዊያን የስራ አጥነት ፎርም መሙላታቸው ኮቪድ 19 በሀገሪቱ ጫናውን እንደቀጠለ መሆኑን ያመላክታል ተብሏል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው በአሜሪካ ለ13 ተከታታይ ሳምንታት የሥራ አጦች ቁጥር ከ1 ሚሊዮን በላይ እየሆነ መመዝገቡ ተስተውሏል፡፡ ይህን ያስተዋለው የሀገሪቱ ማእከላዊ ባንክ አስቸኳይ የኢኮኖሚ ማስተካከያ ካልተደረገ ችግሩ ከዚህም የከፋ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡ ምንም እንኳ አሜሪካ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ተዘግተው የነበሩ […]

የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመግታት የቻይና አፍሪካ ትብብር የማይተካ ሚና አለው አሉ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ለአርትስ በላከዉ መግለጫ  እንዳስታወቀዉ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በዓለም ላይ የተከሰተውን የኮቪድ19 ወረርሽኝ ለመግታት የቻይና አፍሪካ ትብብር የማይተካ ሚና አለዉ ብለዋል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ትናንት “ዓለም አቀፉ የአንድ ቀበቶ አንድ መንገድ ኢኒሸቲቭ” የቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄገበት ወቅት እንዳሉት ፤የዓለም ስጋት የሆነውን የኮቪድ19 ወረርሽኝ ለመግታት በቻይና እና አፍሪካ መካከል የሚደረገው ትብብር ከምንጊዜውም በላይ ወሳኝ ነዉ። ቻይና የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመግታት የተከተለችውን ስትራቴጂ እና የተገኘውን ውጤትም አድንቀዋል። ኢትዮጵያ የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመግታት እያደረገች ባለው እንቅስቃሴ የቻይና መንግስት እና እንደ ጃክማ የመሳሰሉ የቻይና በለሃብቶች እያደረጉት ላለው ድጋፍ ያመሰገኑት አቶ ገዱ፥ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። በኮንፈረንሱ ላይ የቻይና ስቴት ካውንስልና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳትፈዋል። “የአንድ ቀበቶ አንድ መንገድ ኢኒሸቲቭ” ዓለም አቀፍ ትብብርን በማሳደግ የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመግታት የሚያስገኘውን ጠቀሜታ በተመለከተ በስፋት መብራራቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት የላከልን መግለጫ  ያመለክታል።

ኬንያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነት ምርጫን አሸነፈች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012  ቢቢሲ እንደዘገበው ከአፍሪካ ሀገራት ኬንያ እና ጂቡቲ በተወዳሩበት ምርጫ ኬንያ ጂቡቲን 129 ለ62 በሆነ የድምፅ ልዩነት በማሸነፍ ነው የምክር ቤቱን መቀመጫ ያገኘችው፡፡የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጂቡቲን በብርቱ ተፎካካሪነቷ አድንቀው የአፍሪካ ህብረትን ደግሞ ለሀገራቸው ለሰጠው እውቅና አመስግነዋል፡፡ኬንያ ይህን ውድድር ማሸነፏ በአካባቢው ያላት ተሰሚነት ከፍ እያለ የመምጣቱን የሚያመላክት ነው ያሉት […]

በኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት ዴክሳሜታዞን ለኮቪድ 19 ህሙማን እንደ ድንገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወሰነ ።

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012  በኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት ዴክሳሜታዞን ለኮቪድ 19 ህሙማን እንደ ድንገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወሰነ ።የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት ;ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚውለውን ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት በተመለከተ በእንግሊዝ መንግስት የተካሄደውን ጥናት እና ሪፖርት በዝርዝር ተመልክተነዋል ብለዋል፡፡የህክምና ጉዳዮች አማካሪ ቡድናችን እና የጤና ባለሙያዎች አማካሪ ምክር ቤት፣ የሰጠንን ምክረ ሀሳብ […]