loading
የአውሮፓ ፓርላማ በሚቀጥለው ሳምንት በዘረኝነት ጉዳይ ላይ ያተኮረ ውይይት ላደርግ ነው አለ፡፡

የጥቁር አሜሪካዊውን ጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ በርካታ ሀገራ እና ተቋማት በጉዳዩ ላይ ትልቅ ትኩረት ሰጥው መወያያት ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡ ህብረቱ በጥቁሮች ላይ የሚደርሰው ጫና እንዲቆም የሚያደርግ አሰራር ለመዘርጋት እና የዘር መድሎ የሚያደርጉ ግለሰቦችና ቡደኖችን የሚያወግዝ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው በአውሮፓ ህብረት ቁልፍ የሚባሉ ስራዎች የተያዙት ነጭ ቀለም ባላቸው ግለሰቦች ሲሆን ከተመሰረተ ከ60 ዓመታት […]

ህዳሴው ግድብ ላይ የሚደረገው ድርድርድር ከቴክኒክ አንፃር መሰረታዊ የተባሉ ጉዳዮች ቢፈቱም ሙሉ ስምምነት ሆኖ ለመውጣት የሚቀረው ጉዳይ እንዳለ ተገለፀ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2012 ህዳሴው ግድብ ላይ የሚደረገው ድርድርድር ከቴክኒክ አንፃር መሰረታዊ የተባሉ ጉዳዮች ቢፈቱም ሙሉ ስምምነት ሆኖ ለመውጣት የሚቀረው ጉዳይ እንዳለ ተገለፀ:: በመጀመርያ የውሃ ሙሌትና አመታዊ ስራ ላይ ትኩረቱን አድርጎ በኢትዮጵያ በሱዳንና ግብፅ መካከል በቪዲዮ በመታገዝ እየተካሄደ ያለው ድርድር ለሰባተኛ ቀን ትላንት ተካሂዷል።የኢፌዴሪ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዳለው ከሚኒስትሮቹ ውይይት ቀደም […]

በኮሮና ዙርያ የተሰሩ ከ20 በላይ ጥናቶች በኦን ላይን ኮንፈረንስ ለውይይት በመቅረብ ላይ ናቸው ።

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2012 በኮሮና ዙርያ የተሰሩ ከ20 በላይ ጥናቶች በኦን ላይን ኮንፈረንስ ለውይይት በመቅረብ ላይ ናቸው ።የኦንላይን ኮንፍረንሱ ምሁራን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ ያከናወኑዋቸው ጥናቶች ለማሳወቅና ቫይረሱን አስመልክቶ የእውቀት ሽግግር ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።ውይይቱ ላይ የመቐለ አዲስ አበባ ፣ ባህርዳር እና ሃረማያ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን የተሳተፉበት መሆኑን ዶክተር አዲሱ ተናግረዋል ።ጥናታዊ ጽሁፎቹ […]

በአፍሪካ ህብረት የፓን አፍሪካ የእንስሳት ክትባት ማዕከል የኮሮቫይረስን ለመከላከል የሚያደርገውን የምርምር ስራ እንደሚደግፍ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ።

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2012 በአፍሪካ ህብረት የፓን አፍሪካ የእንስሳት ክትባት ማዕከል የኮሮቫይረስን ለመከላከል የሚያደርገውን የምርምር ስራ እንደሚደግፍ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ።የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኙትን የአፍሪካ ህብረት የፓን አፍሪካ የእንስሳት ክትባት ማዕከልና ብሄራዊ የእንስሳት ህክምና ኢንስቲትዩት ዛሬ ጎብኝተዋል።የፓን አፍሪካ የእንስሳት ክትባት ማዕከል በክትባትና መድሃኒት ምርቶች ላይ የሚደረገውን ቁጥጥርና […]

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሚከሰትን የደም አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ የምስራቅ ወለጋ ዞን አመራሮች ደም ለገሱ፡፡

የዞኑ ኮሚኒኬሽን ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ቀደም ሲል የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አገራዊ የደም አቅርቦት በመቀነሱ የልገሳ ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ ነዉ ፡፡ በልገሳ መረሓ ግብሩ የተገኙት የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አስመራ ኢጃራ በሰጡት አስተያየት፤ የኮሮናቫይረስ ከመግባቱ በፊት ሲቀርብ የነበረው ደም በመቀነሱ በችግር ጊዜ ሕዝብና አገርን የማሻገር ሃላፊነታችንን እንወጣለን […]

የተባበሩት መንገስታት ድርጅት ባለፈው ዓመት ብቻ በዓለም 80 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል አለ

የድርጅቱ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ በዓመታዊ ሪፖርቱ ይፋ እንዳደረገው የመፈናቀላቸው መንስኤዎች የርስበርስ ግጭት፣ ጥቃት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ተያያዥ ችግሮች ናቸው፡፡ አልጀዚራ በዘገባው እንዳስነበበው 79.5 ሚሊዮን ከሚሆኑት ተፈናቃዮች መካከል 26 ሚሊዮን ስደተኞች፣ 4.2 ሚሊዮን ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ ከ45 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ናቸው፡፡ በየዓመቱ የሥደተኞች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ያሳሰበው ድርጅቱ በተለይ በየጊዜው የሚከሰቱ ግጭቶች […]

የደቡብ ክልልና አዲሱ የሲዳማ ክልል የስልጣን ርክክብ አካሄዱ

የደቡብ ክልል እና አዲሱ የሲዳማ ክልል በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ፊት ቀርበው የስልጣን ርክክብ አካሄዱ። የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የሲዳማ ዞን በክልል እንዲደራጅ በዛሬው እለት ወስኗል። ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ጉባኤ የሲዳማ ዞን በክልል እንዲደራጅ የወሰነው የሥልጣን ርክብክብ እንዲደረግ […]