loading
የአፍሪካ ልማት ባንክ በፈጠራና በኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ድጋፍ ሊያደርግ ነው

  የአፍሪካ ልማት ባንክ የሳይንስ እና ቴክሎኖጂ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በመርህ በመደገፍ የአፍሪካ ትምህርት ፈንድ በሚል እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጿል፡፡ ባንኩ በአፍሪካ ባለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የበጀት ጉድለት በመሙላትና ተቋማት ውጤታማ ለማድረግ ለአፍሪካ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት ጽኑ ፍላጎት እንዳለው በማላዊ በተካሄደው የሳይንስ እና ቴክሎኖጂ ስብሰባ አስታውቋል፡፡ በባንኩ የትምህርትና የክህሎት ልማት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሄንደሬና ዶቦራ እንደገለጹት […]

ሞቃዲሾ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለ ስልጣን ከሀገሯ እንዲወጡ ትእዛዝ ሰጠች

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በድርጅቱ የሶማሊያ ልዩ ልኡክ ኒኮላስ ሀይሶም ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የምናደርገው በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ በመግባታቸው ነው ብሏል፡፡ ልዩ ተወካዩ የቀድሞው የአልሸባብ ቃል አቀባይ ሸይክ ሙክታር ሮቦውን  መታሰር ጨምሮ ሌሎች የጥትታ ጉዳዮችን አስመልክተው ተደጋጋሚ ደብዳቤዎችን በመፃፍ የስልጣን ገደባቸውን አልፈዋል ብሏል መግለጫው፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሶማሊያ ከእርስበርስ ጦርነት ወጥታ የተረጋጋች ሀገር እድትሆን […]

ፕሬዝዳንት ሺ በታይዋን የመጣብንን አንታገሰውም አሉ

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሽ ጂንፒንግ ታይዋን የቻይና አካል መሆኗን ታሪክም ህግም ይደግፈናል፣ ከአንድ ቻይና ፖሊሲያችን አንድ ጋት አናፈግፍግም ብለዋል፡፡ ሺ ይህን ያሉት ቻይና ከታይዋን ጋር የምታደርገውን ጦርነት አቁማ በሰላም የመዋሀድ ሀሳብ ያቀረበችበትን 40ኛ ዓመት በምታከብርበት ወቅት ነው፡፡ አንዲት ጠንካራ ቻይና ሳይሆን ሁለት ቻይናዎች እንዲኖሩ የሚያሴሩትን ሁሉ አጥብቀን እንቃወማለን ያሉት ፕሬዝዳንቱ ታይዋንን የቻይና አካል ለማድረግ ሁሉንም የእርምጃ […]

የታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለማፋጠን የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ጂኢ ሃይድሮ ፍራንስ ከተባለ ኩባንያ ጋር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ግንባታ ለማፋጠን የሚያስችል ስምምነት መፈራረሙ ተገለጸ፡፡ ጃኢ ሃይድሮ ፍራንስ በቅድሚያ ሃይል እንዲያመነጩ ታስበው ዲዛይን የተደረጉትን ሁለት ተርባይኖችን ጨምሮ አምስት የኃይል ማመንጫ ዩኒቶች ለማምረት፣ ለመግጠምና ለመፈተሸ ኮሚሌክስ ከተባለ ድርጅት ጋር በጥምረት የ53 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዩሮ ስምምነት ፈርሟል። ጂኢ ሃይድሮ ቀደም ሲል […]

321 የቡራዩ ተጠርጣሪዎች ከእስር ሲቀለቀቁ 109 ደግሞ ክስ ተመሰረተባቸው።530 ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጎላቸዋል

የፌዴራል ዐቃቢ ህግ በሰጠው መግለጫ በያዝነው ዓመት መጀመሪያ ላይ በቡራዩ ከተማ በተቀሰቀሰው ጥቃት ተሳትፈዋል ባላቸው 109 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመስረቱን ተናግሯል። ከነዚህም መካከል 81 ተጠርጣሪዎች በተገኙበት 28ቱ ደግሞ በሌሉበት ክስ የተመሰረተባቸው መሆኑን ነው የአቃቤ ህግ መግለጫ የሚያስረዳው፡፡ በቁጥጥር ስር ያልዋሉትን 28 ተጠርጣሪዎች ፖሊስ ለማደን የፍርድ ቤት ማዘዣ እንደወጣባቸው በመግለጫው ተካቷል፡፡ የፌዴራል አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት […]

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአቶ ተስፋዬ ኡርጌና አቶ ማርክስ ፀሃዬ ላይ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ አጠናቆ እንዲያቀርብ የ10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአቶ ተስፋዬ ኡርጌና አቶ ማርክስ ፀሃዬ ላይ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ አጠናቆ እንዲያቀርብ የ10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ