loading
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ወደ ሽሬ አቅንተዋል።

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ወደ ሽሬ አቅንተዋል። ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ሽረ ከተማ ሲደርሱ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የከተማው ነዋሪ ህዝብ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል። ዛሬ ሽሬ ከተማ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የከተማው ነዋሪ ህዝብ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል። ወይዘሮ ዝናሽ በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ለሚሰራ […]

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገር ውስጥ ዲፕሎማቶችን አወያይተያዋል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገር ውስጥ ዲፕሎማቶችን አወያይተያዋል ጠቅላይ ሚር ዐቢይ አሕመድ የሀገር ውስጥ ዲፕሎማቶችን በፅህፈት ቤታቸው ሰብስበው    በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዲፕሎማቶቹ ዓለም አቀፋዊ አዝማሚያዎችን በመረዳት በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ላይ የተመሰረተ ሀሳብና አሠራር ሊመሰርቱ እንደሚገባ በአፅንዖት አሳስበዋል። በተጨማሪም ዲፕሎማቶቹ የመንግስት ፖሊሲን የመተግበር፤ የሚመደቡባቸውን […]

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሴራሊዮን ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር ተወያዩ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሴራሊዮን ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር ተወያዩ፡፡ ሀበሻ ለፍቅር የሚል ማህበር ያቋቋሙት የኮሚኒቲ አባላቱ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በኢትዮጵያ  ስላለው የለውጥ እንቅስቃሴ እና በዳያስፖራው ተሳትፎ፣ እንዲሁም ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡ አሁን በኢትዮጵያ ባለው ለውጥ ደስተኞች መሆናቸውን የገለጹት የኮሚኒቲ አባላቱ ለውጡ በመካከለኛውና በታችኛው እርከንም ሊተገበር ይገባል ብለዋል፡፡ በሀገሪቱ የሚስተዋለውን ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመከላከል […]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በአዲስ አበባ በ43 ሚሊዮን ብር ወጪ የደህንነት ካሜራዎችን እየገጠምኩ ነው አለ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በአዲስ አበባ በ43 ሚሊዮን ብር ወጪ የደህንነት ካሜራዎችን እየገጠምኩ ነው አለ፡፡ በመዲናዋ ከቀይ ሽብር ሰማዕታት ሀውልት  እስከ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አደባባይ ቁጥራቸው 140 የሆኑ የደህንነት ካሜራዎች መገጠማቸው ተነግሯል፡፡ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱልባሲጥ አህመድ፣ የመጀመሪያው ዙር የከተማዋ የደህንነት ካሜራ ገጠማና ስራ 90 በመቶ  ተጠናቋል ብለዋል። ገጠማቸው […]

በካርቱም የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ አልደገፉም የተባሉ አንድ የሃይማኖት አባት ከመስጊድ ተባረሩ

በካርቱም አንድ የሀይማኖት አባት በሀገሪቱ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ባለመደገፋቸው ህዝቡ ከመስጊድ አባርሯቸዋል ተባለ ። ሱዳን ውስጥ ካሉ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀይማኖታዊ መሪዎች አንዱ የሆኑት ኢማም አብዱል ሀይ ዩሱፍ  ተቃውሟውን  እየመሩ አይደለም በሚል ከአማኞች በቀረበባቸው  ውንጀላ  ነው ከመስጊድ  የተባረሩት። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በተለቀቀ ተንቀሳቃሽ ምስል፤ መንግሥትን በመደገፍ የሚታወቁትን  እኚህን ኢማም አንድ ግለሰብ ሲቆጣቸው ታይቷል። ሮይተርስ እንደዘገበው ባለፈው አርብ […]

የኖቤል ተሸላሚው ሳይንቲስት በዘረኛ ንግግራቸው ማዕረጋቸውን ተቀሙ

የኖቤል ተሸላሚው ሳይንቲስት በዘረኛ ንግግራቸው ማዕረጋቸውን ተቀሙ አሜሪካዊው ሳይንቲስት ዶክተር ጄምስ ዋትሰን በአንድ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ ዘረኛ ንግግር ካደረጉ በኋላ  ማዕረጋቸውን ተነጥቀዋል። በዘረ መል ምህንድስና ምርምር የሚታወቁት የኖቤል ተሸላሚው ሳይንቲስት የጥቁሮችና የነጮች ዐዕምሮ ምጥቀት በዘረ መላቸው ይወሰናል የሚል ዘረኛ ንግግር አድርገዋል። ሳይንቲስቱ እንደ አውሮፓውያኑ  አቆጣጠር በ2007 ተመሳሳይ ዘረኛ አስተያየት ሰንዝረው ይቅርታ ጠይቀው ነበር።

ባለሀብቶች የግብርና ምርቶችን የሚሰበስብ የሰው ኃይል አጣን አሉ፣ ምክንያቱ ደግሞ የፀጥታ ችግር ነው ብለዋል።

ሰፋፊ እርሻዎች ባሉባቸው አካባቢዎች በየጊዜው እያጋጠመ ያለው የፀጥታ መደፍረስ በፈጠረው ሥጋት፣ ባለሀብቶች የግብርና ምርቶችን የሚሰበስብ የሰው ኃይል ማግኘት አልቻልንም እያሉ ነው፡፡ በተለይ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በጋምቤላና በአፋር ክልሎች ምርት መሰብሰብ በነበረበት ጊዜ እያጋጠመ ያለው ግጭት፣ የሰው ኃይል ወደ ሥፍራው እንዳይንቀሳቀስ አድርጓል  ነው ያሉት ባለሀብቶቹ፡፡ የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የጥጥ ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ […]

የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች ለዘላቂ ሰላምና ሃገር ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች ለዘላቂ ሰላምና ሃገር ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ። ከመላው ሃገሪቱ የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች የተሳተፉበት ሃገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል ፡፡ በኮንፈረንሱ ላይ ለወጣቱ ትውልድ ሃገራዊ እሴቶችን በማውረስ ዘመናዊነትን በጥበብ እና በብልሃት እንዲላበስ፥ የሃገር ሽማግሌዎች ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል አሳስበዋል። ሚኒስትሯ የሃገር ሽማግሌዎች ሰላምን ከማስፈንና […]