loading
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ደደቢት ከሊጉ መሰናበቱን ሲያረጋግጥ፤ ጊዮርጊስ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት መርሀግብር ጨዋታዎች፤ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በአዲስ አበባ እና ክልል ስታዲየሞች ላይ ተካሂደዋል፡፡ ትናንት አዲስ አበባ ላይ የምስራቁን ድሬዳዋ ከነማ ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ 2 ለ 0 ድል በማድረግ ወደ ድል ጎዳና መመለስ ችሏል፡፡ ፈረሰኞቹ መረብ ላይ ያሳረፏቸው ሁለት ግቦች በተከላካይ መስመር ተሰላፊው አስቻለው ግርማ የፍፁም ቅጣት ምት ጎሎች ተገኝተዋል፡፡ የመጀመሪያው አጋማሽ […]

ዛማሊክ የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ አሸናፊ ሆነ፡፡

የ2018/19 የቶታል ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ የመልስ ግጥሚያ ትናንት ምሽት ግብፅ ላይ ተካሂዷል፡፡ የፍፃሜው ጨዋታ ደግሞ ግብፁ ኤል ዛማሊክ እና የሌላኛዋ ሰሜን አፍሪካዊት ሀገር ሞሮኮ ተወካይ ሬነሳንስ ስፖርቲቭ ዴ ቤርካኔ መካከል ዛማሊክ በመለያ ፍፁም ቅጣት ምት 5 ለ 3 በመርታት በታኩ የመጀመሪያውን የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ አሳክቷል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ሳምንት ሞሮኮ ላይ የመጀመሪያ ግጥሚያቸውን አድርገው፤ […]

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላትና የእስልምና ኡለማዎች የኢፍጣር የእራት ግብዣ አደረጉ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላትና የእስልምና ኡለማዎች የኢፍጣር የእራት ግብዣ አደረጉ፡፡