loading

ለሁለት ቀናት በስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምንጮች ላይ የተካሄደው ውይይት ተጠናቀቀ የስፖርታዊ ጨዋነት ምንጮች በሚል በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የተዘጋጀው ፕሮግራም ባለፉት ሁለት ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ትናንት ተጠናቅቋል፡፡ በውይይቱ የሁለት ቀናት ቆይታ ስለ ስፖርታዊ ጨዋነት በባለድርሻ አካላት መካከል ምክክር ተደርጓል፡፡ አጠቃላይ ውይይቱ ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት በኩል በተሰጡ የማጠቃለያ ሀሳቦች የአቋም መግለጫ ተጠናቅቋል ፡፡ ከመንግስት በኩል […]

የአፍሪካ ህብረት የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ስልጣን የሚያስረክብበትን ቀነ ገደብ አራዘመ፡፡

የአፍሪካ ህብረት የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ስልጣን የሚያስረክብበትን ቀነ ገደብ አራዘመ፡፡ የአፍሪካ መሪዎች በሱዳን እና በሊቢያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር ካይሮ  ላይ በተገናኙበት ወቅት ነው ውሳኔው የተላለፈው፡፡ ህብረቱ ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ ወታደራዊ ምክር ቤቱ በ15 ቀናት ውስጥ ስልጣኑን ለሲቪል የሽግግር መንግስት እንዲያስረክብ ይህ ባይሆን ግን ሱዳን ከህብረቱ እንደምትባረር አስጠንቅቆ ነበር፡፡ የግብፁ የዜና ወኪል ሜና […]

ሱዳናዊያን በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት በሰላማዊ ውይይት መፍታት ይበጃቸዋል ሲሉ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ

ሱዳናዊያን በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት በሰላማዊ ውይይት መፍታት ይበጃቸዋል ሲሉ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ ምክተል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ጥሪ ያቀረቡት በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ እየመከረ ባለው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ውይይት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ንግግራቸው የሱዳን ፖለቲከኞችና ባለድርሻ አካላት በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት በሰላማዊ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ዥንፒንግ የሁለትዮሽ ውይይት አካሄዱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የልዑካን ቡድናቸው ከቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ዥንፒንግ ጋር ከቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ በፊት የሁለትዮሽ ውይይት አካሄዱ የጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድን አመራርና ያለፈውን አንድ ዓመት የኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት እንደሚያደንቁ የገለጹት ፕሬዚዳንት ዥንፒንግ ቻይና ለኢትዮጵያን ዕድገት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች ብለዋል:: በውይይቱ ወቅትም እስከ የፈረንጆች 2018 ዓ.ም መጨረሻ የተጠራቀመ የብድር ወለድን ሙሉ በሙሉ እንደተሠረዘ አስታውቀዋል:: ከዚሁም […]

የቻይና የኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን ኢትዮጵያ ውስጥ መስራት እፈልጋለሁ አለ

በእስያ ትልቁ የኤሌክትሮኒክስ አምራች የሆነው የቻይና የኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ በከተሞች ዝመና እና በዜጎች ደህንነት ጥበቃ ላይ የቴክኖሎጂ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ። የቻይና የኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን ምክትል ፕሬዝደንት ሊ ሊጎንግ በኢትዮጵያ የከተማ ዝመና ‹‹ስማርት ሲቲ››፤ በዘመናዊ የትራፊክ ቁጥጥር እና በዜጎች ደህንነት መጠበቂያ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግም ቃል ገብተዋል።   ኩባንያው ይህንን ይፋ ያደረገው በኢኖቬሽንና […]

ልጣን ላይ ያሉትና የቀድሞ የአፍሪካ መሪዎች ለ8ኛዉ የጣና ከፍተኛ የደኅንነት ፎረም ባህር ዳር ከተማ ሊገናኙ ነው

በስልጣን ላይ ያሉትና የቀድሞ የአፍሪካ መሪዎች ለ8ኛዉ የጣና ከፍተኛ የደኅንነት ፎረም ባህር ዳር ከተማ ሊገናኙ ነው። መሪዎቹ ባህር ዳር የሚገናኙት በአፍሪካ ቀንድ ሁኔታዎች ላይ ለመምከር ነው። ”የፖለቲካ ተለዋዋጭነት በአፍሪካ ቀንድ እና የታዩ የሠላም ጅማሮዎችን ማጎልበት” በሚል መሪ መልክዕት የሚካሄደው ይኸው ፎረም ከሚያዚያ 26-27 ድረስ ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድ ነው ማወቅ የተቻለው። የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር […]

ቻይና እስካለፈው የፈረንጆች 2018 ድረስ በኢትዮጵያ ላይ የተጠራቀመውን የብድር ወለድ ሙሉ በሙሉ ሰረዘች

ቻይና እስካለፈው የፈረንጆች 2018 ድረስ በኢትዮጵያ ላይ የተጠራቀመውን የብድር ወለድ ሙሉ በሙሉ ሰረዘች። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቻይና የቤልት ኤንድ ሮድ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ቤጂንግ እንደሚገኙ ይታወቃል። በጉብኝታቸው ከቻይናው ፕሬዚዳንት  ሺ ጂንፒንግ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማካሄዳቸው ይታወቃል። የእዳ ስረዛው ይፋ የሆነውም ይህንኑ ውይይት ተከትሎ ነው ተብሏል። አንዳንድ ምንጮች እንደሚጠቅሱት ኢትዮጵያ 20 ቢሊዮን ዶላር የቻይና […]