loading
የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል የማዛወሩ እቅድ የሚፈለገውን ውጤት አላስገኘም ሲሉ አንዳንድ ሰራተኞች ቅሬታ አቀረቡ

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ወደግል ሲዘዋወሩ መንግስት ለሰራተኞቹ እና ለድርጅቱ ተገቢውን ክትትል እንደማያደርግ ወደ ግል የተዘዋወሩት እና ለኪሳራ የተዳረጉት ድርጅቶች ለአርትስ ገልፀዋል፡፡ በተቃራኒው መንግስት የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደግል ባለሃብቶች  ሳዘዋውር በጥንቃቄ እና በክትትል  ነው ይላል፡፡ በመንግስት ስር የሚገኙ  እንደ ባቡር ፣ የስኳር ልማት፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የሆቴልና የተለያዩ የማምረቻ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በአክሲዮን ሽያጭ ወደ […]

በእንግሊዝ የጦርሃይል ሙዚየም የተቀመጠው የአጼ ቴዎድሮስ ጸጉር በነገው ዕለት ለኢትዮጵያ ይመለሳል

የአጼ ቴዎድሮስን ጸጉር ለማስመለስ ጥረት መካሄድ የጀመረው ከረጅም ጊዜ በፊት ቢሆንም በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍስሃ ሻውል ከእንግሊዝ ብሄራዊ ሙዚየም ዳሬክተር ብርጋዴር ጀስቲን ማሴጄውስክ ጋር ከተወያዩ በኋላ በእንግሊዝ በኩል የአጼ ቴዎድሮስን ጉንጉን ለኢትዮጵያ ለመመለስ ስምምነት ላይ ተደርሷል። የሁለቱ ሃገራት ሃላፊዎች በዚህ ቅርስ የመመለስ ሂደት ላይ የንጉሰ ነገስቱን ክብር በሚመጥን መልኩ በሚካሄደው የሽኝት ስነስርዓት ላይ በሰፊው መክረዋል፡፡ […]

በቦሌው የቡድን ጸብ ተካፋይ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች በሙሉ ተገቢው ምክር ተሰጥቷቸው መለቀቃቸውን ፖሊስ አስታወቀ

በተለምዶ ቦሌ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተከስቶ በነበረው የቡድን ጸብ ላይ ተሳትፈዋል በማለት በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን ተጠርጣሪዎች ሙሉ በሙሉ መልቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታወቀ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የኢንዶክትሪኔሽን እና የህዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት ተፈጥሮ የነበረው የጸጥታ ችግር ተራ የቡድን ጸብ እንጂ ብዙዎች በማህበራዊ ሚዲያ እንዳራገቡት ከፖለቲካ ግጭት […]

የአደጋው ምክንያት የአውሮፕላኑ የቴክኒክ ችግር ሆኖ ከተገኘ ቦይንግ ለሟቾች ከባድ የካሳ ክፍያ መፈጸም ይጠብቀዋል እየተባለ ነው

በሰሞኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ኢቲ 302 የተመዘገበውና ቢሾፍቱ አካባቢ የመውደቅ አደጋ የደረሰበት ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ምርመራ ሲጠናቀቅ የአደጋው ምክንያት የአውሮፕላኑ የቴክልኒክ ችግር ሆኖ ከተገኘ ቦይንግ ኩባንያ ለደረሰው የሰው ህይወት ህልፈት ከባድ ካሳ ከፍያ ይጠብቀዋል እየተባለ ነው። እስከአሁን የወጡት መረጃዎች ከአሜሪካው አዲሱ  የቦይንግ አውሮፕላን ምርት የቴክኒክ ችግር ጋር የተያያዘ  እንደሆነና  ከ6 ወራት […]